ጎንደር ላይ በተደረገው ታሪካዊ ሰልፍ የተነቃቃው የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግሉን ከዳር ያደርሰው ዘንድ የመታገያ ጣራውን ጎንደሮች ከፍ አድርገው ሰቀለውታል፥

የኢትዮጵያ ትንሳኤ እንዲፋጠን፥ በሁሉም የአገሪቱ ክፍል ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች እንጠብቃለን።
በጎንደር የተጀመረውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት፥ ወያኔ የዘር ፖለቲካ ለማድረግና አወላግዶ ለማቅረብ ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም የጎንደር አማራ ፍጹም ኢትዮጵያዊነት የተንጸባረቀበት ሰላማዊ ተቃውሞ በማድረግ የወያኔን ከፋፋይ ዓላማ ከንቱ አድርጎበታል። ..
የጎንደሩ የአማራ ተጋድሎ፥ የማንኛውም ዜጋ ማንነትና የግል መብት እንዲከበር በሰላም የተጠየቀበት፥,,,,,,,,,,,የሁሉም ኢትዮጵያውያን ጉዳይ የሆነውን የነጻነት ትግል ከፍ አድርጎ ከብሄር፣ ከቋንቋና ከሃይማኖት የላቀ ኢትዮጵያዊ አጀንዳ ያላበሰ፥ ,,,,,,,,ከማንኛውም የውጭ ኃይል ነጻ በሆነ መንገድ ሕዝቡን ብቻ ይዞ፥ ግፍኛውንና ዘረኛውን የወያኔን አገዛዝ ቢቻል በሰላም ባይቻል በግድ ታግሎ ለመቀየር በቁርጥኝነት የተነሳ፥ በመላው ኢትዮጵያ ለሚንቀሳቀሱ ነጻነት ፈላጊ ሁሉ አጋርነቱን ያሳየ፥ ባለታላቅ ራዕይ መሆኑን በአደባባይ አስመስክሯል።

የጎንደሮች የተቃውሞ ሰልፍና የአማራ የማንነት ጥያቄ ሓምሌ 24 ቀን አስደናቂ በሆነ ድርጅታዊና ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ተደርጎ በሰላም በመጠናቀቁ፥ የኢትዮጵያን የነጻነት ትግል ወደ አዲስ ምዕራፍ በማሸጋገር በኢትዮጵያ የትግል ታሪክ ውስጥ ከሚመዘገቡት አንዱ ሆኖ ይኖራል።
ጎንደር ዛሬም እንደገና ታሪክ ሰራ፥
ይህ ነው ጀግንነት፥ የቴዎድሮስ አገር፣ የጣዓይቱ አገር፣ የፊታራሪ ገብርየና የታንጉት አገር ጎንደር የጀግና አገር፥
ጎንደር ዱሮም በአንድነቱ ላይ የማያወላዳ አቋም ያለው፥ ለክፉ ቀን የሚደርስ፥ ለተጠቁት የሚቆም ክቡር ሕዝብ ነው።
ትግሉ እስከ ድል አደባባይ ነው።
ጎንደር የተጀመረው ገድል፥ በባህር ዳር፣ በደብረብርሃን፣ በደሴና በአዲስ አበባ ይቀጥላል፥
ከሰሜን ጎንደር ወደ ደቡብ ጎንደር ይዛመታል፥ ተጀመረ እንጂ ገና ዓላለቀም፥

13873098_1717889688463205_8628392187762145814_n 13876146_10155041111295744_3791289748273407227_n 13912565_10155041111285744_289411231563913915_n 13912737_10155041111345744_752584979657186182_n

Posted on August 1, 2016, in Andinet party, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: