ይድረስ ለመላው ኢትዬጵያዊ ወገናችን ሁሉ! እነሆ ወሳኙ የፍልሚያና የትንቅንቁ ወቅት ላይ ደረስን

August 17, 2016

በስራኤል ሃገር ከምንገኝ የጎንደር ተዎላጆች ማህበር

በባእዳን እጆች ተደግፈው፤ በስልጣን ላይ የነበረውን የደርግን ድንቁርናና አልሰማባይነት የተፈጠረውን ክፍተት ተጠቅመው ላለፉት ሃያ አምስት የመከራ ዓመታት በመንበሩ ላይ ፊጥ ያሉት የባንዳ ልጆች በመዘዙት የበቀል ጅራፍ ያልተወጋና ጠባሳው የማይገኝበት የሃገር ልጅ ይኖራል ብሎ ማሰብ በእጅጉ የዋህነት ነው ኦሮሞው፤ አማራው፤ ጉራጌው፤ ሱማሊው ፤ ትግሬው በጠቅላላ ሁሉም ኢትዬጵያዊ የእዚህ የህወሃት መርዘኛ ፖለቲካ ሰለባ ነው።  ምክኒያቱም ይህ ለኢትዬጵያዊነት የሚከፈል ልዩ ዋጋ ነው ለእነርሱም ይህ የባንዳነት ማረጋገጫቸው ነው  “ወይራ ዶግ ይወልዳል” ሆነና እነአሉላ በወጡበት ማህጸን እነመለስ እና እነ ስብሃት ወጡ፤ የኢትዬጵያዊነት መሰረት ከሆነው ከትግራይ ህዝብና መሬት ተፈለፈሉ ዘይገርም ነው ነገሩ!።

GondarProtest102

እርግጥ ነው እነዚህ  የበግ ለምድ ለብሰው የመጡ የህወሃት ተኩላዎች ራሱን የብርሃን መልዓክ እስኪመስል መቀየር ከሚችለው ክፉውና መሰሪው አባታቸው ከዲያብሎስ በተካፈሉት ጥበብ ከክፋት በቀር  አንዳች መልካም ነገር በማይገኝበት ማንነታቸው ሃገራችንን የሲዖል ምሳሌ ማድረጋቸው ህሊናቸውን ከደፈጠጡትና ለቦርጭ ከሚሮጡት ውጭ ለማንኛውም ኢትዬጵያዊ ግልጥና ግልጥ ነው። እነዚህ የሌዋታን ውላጆች በረጩት መርዝ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የተጠቀሙበት ስልት በተለይም በሁለቱ ታላላቅ ህዝቦች  ማለትም በሰፊው የኦሮሞና የአማራ ህዝቦች መካከል ለጊዜውም ቢሆን የተሳካ መስሎ ታይቶም ነበር ይሁን እንጅ በእውነተኞቹ ኢትዬጵያዊያን ያላሰለሰ ጥረትና የላቀ መስዋዕትነት እነሆ ዛሬ ላይ ሁለቱ ወንድማማቾች የእባቦቹን መርዞች አርክሰው ከልብ የተቃቀፉበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ይህ ድል ህወሃትን ያስደነበረ ቀሪውን ኢትዬጵያዊ ደግሞ ያስፈነጠዘ ድል ነው ይህን ድል የመጠበቅ ሃላፊነት ደግሞ በእያንዳንዱ ዜጋ ትከሻ ላይ መውደቁን ልናውቅ ይገባል።

ምልክቱን በባንዲራችን ላይ ካስቀመጡለት ከሉሲፈር ጋር በደደቢት ቃልኪዳን የተጋቡት ሊዋታኖቹ ኃይልን የሚሞሉት ደግሞ ከዘንዶው ነው እነርሱ የደም ግብር ያቀርቡለታል እርሱ ጊዜያዊ ኃይል ይሰጣቸዋል ፤ ህዝብን ያደነዝዝላቸዋል የዕምነት መሪዎችን የሃሰት ትንቢት እንዲናገሩ ያስታቸዋል ከግዚአብሄር ሃሳብ ጋር ፈጽሞ የሚጣረስ ትምህርት እንዲያቀርቡ ያመቻቻቸዋል።  ይህ ዘንዶ ምንም እንኳን እስከተቀጠረለት ቀን ድረስ በዘመናት መካከል ምድራችንን ቢተናኮለም ዋናውን ሰራ የጀመረው ግን በዓድዋ ዘመቻ ጊዜ ነበር በወቅቱ በአባቶቻችን ክንድ ጅራቱ እንደተቆረጠ አመለጠ። እንደገና ከአርባ ዓመት በኃላ መርዙን ተሞልቶ እየተጎተተ የመጣው ኃይል ብዙ ዋጋ ካስከፈለን በኋላ አሁንም በአባቶቻችን ፈታኝ ትግል ተመትቶ ተመልሷል። አሁን ግን በስመ ወያኔነት ቆዳውንም ቀይሮ መርዙን በብዙ እጥፍ ጨምሮ መጥቷል። እነሆ ይህንን አስጨናቂ ዘንዶ እግዚአብሄር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይቀጣው ዘንድ ንጉሱ በደጅ ነው (መዝ 74 ፤ 13-14) “ አንተ የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ ለኢትዬጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።” ይላል። እግዚአብሄር ይህንን የህወሃት ስጋ ለብሶ የተገለጠን ዘንዶ የሚመታበት ጊዜ ላይ ነን ሁል ጊዜ ህዝብን እያስጨነቀ እያስለቀሰ እንዲኖር አይፈቅድለትም። አዎ ያንድ ነገር መነሻ እንዳለው እንዲሁ መድረሻ አለው ፤ የመዝራት ጊዜ አለ የማጨድ ጊዜ አለ። መከራን ዘሩ ምን ያጭዱ ይሆን? ፤ ውሸትን ዘሩ ምን ይሰበሰቡ ይሆን፤ ትዕቢትን ዘሩ ምን ያከማቹ ይሆን?

በአስራ ዘጠነኛው መግቢያ ዓመታቶች ላይ  አሜሪካንና ህዝቧን ህልውናቸውን አደጋ ላይ የሚጥል የወንበዴ መንጋ ምክኒያት በትርምስ  በእጅጉ ተናውጣ ነበር ይሁን እንጅ  ችግሮቻቸውን  በራሳቸው መፈታት የሚያውቁበቱ ነጮቹ ያን የጨለማ ወቅታቸውን በድርሳን ለብደው ዳግመኛ እንዳይነሳ አድርገው ቀበሩት። ታዲያ ይህንን አስጨናቂ ጊዜ ጸሃፊ Eugene Rosow ሲገልጠው “ The Born To Loss” ብሎ መጽሃፉን ሰየመው የጥፋት ልጆች እንደማለት ነው።  እነዚህ እርጉም ሃዋርያትና የጥፋት መልዕክተኞች በነዚህ ሃያ አምስት የመከራ ዓመታት የጉስቁልናን ምንነት አሳዩን ፤ የሃዘንን ዶፍ አጠገቡን፤ የውርደትን ጥግ አስጨበጡን፤ የመለያየትንም ጣራ አስነኩን ምን ያልሆንነው አለ? በጠመንጃ የገሩት ሚዲያቸው ጥቁሩን ነጭ፤ ገደሉን ሜዳ፤ ምድረበዳውን ገነት የሚልና እነርሱ መስማት የሚፈልጉትን ብቻ እንዲናገር አድርገው ቃኙት ። እናም በዚሁ በቀቀን በሆነው ሚዲያቸው የግልብጥ እያናገሩ የተራበውን ጠግበሃል፤ የመነጠውን ድሃ በልጥገሃል፤ በጠመንጃ ዘር እየፈጁ ዲሞክራሲ አሰፈንልህ እያሉ በመላገድ በታላቁና በኩሩው የኢትዬጵያ ህዝብ ላይ ተዛበቱበት ግን ይህም ያልፋል አዎ ያልፋል!  የሃፍረት ታሪካችን ቢሆንም እንኳን ግን ደግሞ የማይደገም ታሪክ ሆኖ ይመዘገባል።

ውድ ወገናችን ሆይ ዛሬ ላይ የግፉ ጽዋ ሞልቶ በአርያም ፈሧል። አባቶቻችን ወንድ ልጅ ሲፈራ ያዩት እንደሆነ ” በላ ተመልሰህ ከእናትህ ማህጸን ግባ”  ይሉታል። ወዴትስ ይኬዳል ? ከዚህ በላይስ የውርደትን ገጣባ ተሸክሞ ከምድር በላይ የመኖር ትርጉሙስ ምንድነው? ይህችን ውብ ሃገርህን እንደአባቶችህ በክብር  አስጠብቀህ ታሪክ በመስራት ለመጭው ትውልድ ታስተላልፋለህ? ወይንስ ያ መላው ጥቁር ህዝብ እንደ ትልቅ ተስፋ አንጋጦ የሚያየው ኢትዬጵያዊነት በአንተ ዘመን ያበቃለታል? እናም መምጫህ የማይታወቅ ከርታታ ሆነህ ታልፋለህ? ቆም በልና አስብ የሰው ልጅ ክብሩ ታሪኩ ነው። ሃገርህ ክብርህ ናት ሃገርህ ከሞተች ያንተም ነገር እዚያው ላይ ያበቃለታል። አባቶቻችን ከምንም በላይ ሃገር ነው ሲሉና በስንኝ ሲሸበልሏት እንዲህ እንዳሉ ተመልከት ፤-

እናት አባት ቢሞት በሃገር ይለቀሳል፤

ሃገር ከሞተ ግን ወዴት ይደረሳል?

ጥቅል ሃሳቡ ማዕረጉም ክብሩም በሃገር ነው ለማለት ነው።  ዛሬ ይህቺ የአፍሪካ ንግስት ፤ የጥቁር ህዝብ ፈርጥ፤ የረጅም ታሪክ ባለቤት ኢትዬጵያ  በባንዳና ወሮበላ የትግራይ ልጆች ታሪኳን እንዳልሆነና እንዳልነበረ ለማድረግ የመጨረሻው ጫፍ ላይ እንገኛለን ። ስለዚህም ሁላችንም ቀበቶአችንን ጠበቅ ትንፋሻችንን ዋጥ አድርገን በበቀል ከተሞሉ የባንዳ ልጆች ጋር እየተናነቁ እየወደቁም እየጣሉም ከሚገኙት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር አብረን ልንቆም ይገባል። ትግላችንን ለድል ለማብቃት የሚከተሉት መርሆዎች አስፈላጊ ናቸው ብለንም እናምናለን። ጠንካራ ዲስፕሊን፤ ከአጉል ጥላቻ የራቀ ሰፊ ልብ፤ የራሳችን ስራ በአግባቡ መወጣታችንን ማረጋገጥ እንጅ ሌሎችን የትግል አጋሮቻችን ከመወንጀል መቆጠብ፤ ወንጀለኛውን የህወሃት ቡድን ከሰፊው የትግራይ ህዝብ ነጥሎ ማየት መቻል ምክኒያቱም ቡድኑ ብቻውን ተነጥሎ እንዳይቆም የትግራይን እንደማምለጫ ምሽግ ለመጠቀም ተግቶ እየሰራ በመሆኑ በዚህ በኩል ንቁዎች  ልንሆን ይገባል።

ለተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፤-  ይህ ወቅት በአንድ ቆመን ራሳችንን እየገዛን ፤ ከየትኛውም  የግል መሻትና አጉል ምኞት በፊት ሃገርና ህዝብን በማስቀደም  በአንድ ማዕከል ስር የሚመራ ጊዜያዊ ተቋም በመፍጠርና በሳል አመራር ለመስጠት ራስን ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው። ይህ አሰራር መጠነኛም ቢሆን አሁን የሚታየውን  የቅንጅት ክፍተት በመሸፈን ገንፍሎ የወጣውን የህዝብ ብሶት ለድል ለማብቃት በእጅጉ ይረዳል ይህን ስራ በአግባቡ ለማከናወንም ያለዕረፍት ብዙ መሰራት ይጠበቅብናል ብለን እናምናለን። እንዲህ ዓይነት ተቋም መፍጠር ያላግባብ የሚባክንን የህዝብ ንብረትና ጊዜ ከመታደጉ ሌላ አቅጣጫችን ከሚያስቱት መልቲዎችም ይሰውረናል። ይህ ወቅት ከመጠላልፍ ጌም ወጥተን ከዚያ ይልቅ የጠሩ ሃሳቦችን በማፍለቅና በጠንካራ ዲስፕሊን በመታገዝ የወገንን ስቃይና ጣር ለመቀነስ ፊተኛ ሆነን በመገኘት ለቤዛነት ራሳችንን ማዘጋጀት የሚጠበቅብን ጊዜ ነው። የትግሉ ባህሪ ይህንንም ይጠይቃልና!። አዎ ይህ ወቅት ወሳኝ ወቅት ነው  እርስ በርሳችን በመቀራረብ ተደጋጋፊ የሆኑና  የተሰናሰሉ ስራዎችን በመስራት በአሸናፊነት ለመወጣት ዕረፍት የለሾች ልንሆን ይገባል።  ይህንን በህዝብ የቁጣ ማዕበል የታጀበ የአመጽ ግለት ሳይቀዘቅዝና አንዳች ደባች አዚም ጥላውን ሳይጥለበት ከመጋኞቹ ነጥቀን በህዝብ እጅ ለማስቀመጥ በመለኮታዊ ጥበብ ሳይቀር የተካንን ልንሆን ይገባል።

የ1997 ዓም ሃገር አቀፍ ምርጫ ብዙ አስተምሮን አልፎአል ። ህዝብ ዘረኞቹን  የህወሃት ወንበዴዎች ለቦታው አትመጥኑም ብሎ በካርዱ የቀጣበት ጊዜ ነበር። ይሁን እንጅ በእኛ የውስጥ ድክመትም ይሁን በምዕራባውያን የረቀቀ ተንኮል የህዝብ ትግልና መስዋዕትነት ጭቃ ላይ ተደባልቆ የብዙዎቻችንን ልብ ሰብሮ አልፎአል ያ ውድቀታችን እንዳይደገም ምን እናድርግ? ህዝብ በባዶ እጁ ወደ አደባባይ በመውጣት ዘመናዊና ገዳይ መሳሪያዎችን እስከአፍንጫው ከታጠቁ ጨካኝ የባንዳ ልጆች ጋር ፊት ለፊት እየተጋፈጠ ባለበት በዚህ ወቅት መስዋዕትነታችንን ለመቀነስ  ምን ዓይነት የረቀቁ ዘዴዎችን እንፍጠር? ይህንን አስቸጋሪ ወቅትስ እንዴት እንለፈው? ማሰብ ፤ ማሰብ አሁንም ማስብ ከዚያም በድርጊት መቋጨት ወቅቱ የሚጠብቀው ተግባራችን ነው።

በትግሉ እሳት ውስጥ ለምታልፉ ለሃገራችን  የኢትዬጵያ ልጆች፤-   ውድ ወንድሞቻችን ፤ እህቶቻችን ፤ እናቶቻቸን፤ አባቶቻችን እንዲሁም ልጆቻችን የምታልፉበትን እሳት እየተመለከትን በሚደርስባችሁ በደልና አፓርታይድን ባስናቀ የግፍ መዓት ውስጣችን እየነደደ አለን ግን አብረናችሁ ነን። አንዳንድ ጊዜስ ውጭ ሆኖ ከመቃጠል አብሮ በሳቱ ውስጥ ማለፍ ሳይሻል አይቀርም ይሁን እንጅ ውጭ ሆኖ በእሳት ውስጥ ለሚያልፈው ህዝብ ሃሳብ መስጠት ህሊናንና የሚፈትኑ የሞራል ጥያቄን የሚያጭሩ ሁኔታዎች ቢኖሩም ምንም ማድረግ አይቻልም ሃሳብ ከመስጠትና  በሚያስፈልገው አብሮ ከመቆም ውጭ ሌላ አማራጭ የለንም።

በዚህ አጭር ጽሁፍ ላማሳሰብ የምንወደው ወጣቶቹ ብሩህ የሆነውን አዕምሮአችሁን በመጠቀም እስካሁን ባደረጋችኋቸው እንቅስቃሴዎች  እንዳስደመማችሁን ልንነግራችሁ እንውዳለን  ለዚህ ምስክር የሚሆነን  በቅርቡ በአማራ በኦሮሚያ የተደረጉት ሰላማዊ ሰልፎች ናቸው እጅግ የሚያስደንቁ፤ ኢትዬጵያዊ ጨዋነትን የተሞሉ ፤ ብስለት የታየባቸው ነበሩ በዚህም ስራ ልትኰሩ ይገባል ይሁን እንጅ ባገኛችኋቸው ድሎች በመስከር ወደ ፍጻሜው ከመገስገስ እንዳትዘናጉ እጅግ ጥንቃቄ ያሻል ። የወደፊቱን  ትግላችሁንም  እንዲሁ በቅንብሮች ረቂቅነት የህዝቡን ኃይል በአግባቡ መጠቀም፤ ጥይቶችን በማክሸፍ የተጎጅውን ቁጥር በመቀነስ፤ በተለያዬ ባሉ አውራጃዎችና ወረዳዎች የማያቋርጥና የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር ጉጂሌውን ማስጨነቅ ይቻላል ይህ አሰራር በትራንስፖርት የሚሯሯጠውን የወያኔ ደም አፍሳሽ አጋንንት ለመገደብ በእጅጉ ይረዳል ሲያልፍም ጫናው ከበዛም ዱርቤቴ ለማለት ነፃ መሬት ለማግኘት ዓይነተኛ መፍትሄ ነው። ከዚህ ወዲያ ወዴት ይደረሳል? እስከመቼ ስደት? እስከመቼስ ለባንዳ ልጆች ተሽቆጥቁጠን? በቃ ምን ይደረግ ይህ ተጋድሎ በዘመናችን ሰርተነው እንድናልፍ ታሪክ የጣለብን የቤት ስራችን ነው።  እናም ጌም ስራባቸው እንጅ በከንቱ ደምህን እያፈሰሱ ለአጋንንታቸው መስዋዕት እንዲያደርጉህ አትፍቀድላቸው አንተ እኰ የዬቶር ልጅ ነህ ደግሞም ከእንግዲህ ወደ ኋላ መመለስ የባርነት ሰንሰለታችንን ለማጥበቅ እንጅ ሌላ መፍትሄ የለውም  እናም በርቱ!!!።

ለኦርቶዶክስና ፕሮቴስታንት መሪዎችና ተከታዬች፤  ይህ ወቅት በመዘናጋትና በቸልተኝነት ለህወሃት መሰሪ ፕሮፐጋንዳ ታልፈን የምንሰጥበት ጊዜ እንዳይሆን አጥብቀ የምንመረምርበት ወቅት ነው መጽሃፉም የሚለው እንኳንስ የፖለቲከኞችን መሰሪነት ትንቢትን ሳይቀር መርምሩ ነው የሚለው። እውነት ወዴት ነው? ህዝባችን ሲገደል ዝም፤ ሲታሰር ዝም፤ ሲሰደድ ዝም፤ ሃገር ያለ ሃይ ባይ ስትዘረፍ ዝም የትኛው የክርስትና መጽሃፍ ነው ይህንን የሚያስተምረን? ነው ወይስ ፍርሃትን በመንፈሳዊ ካባ መሸፈን? የዓለም መድኃኒት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ላይ የወጣበት ጥጉ ነገር እኮ እውነት ነው እንዲያውም ተልዕኮውን ሲገልጽም እውነት እኔ ነኝ ስለ እውነትም ልመሰክር መጣሁ ነው ያለው ። ታዲያ ተከታዬቹ ወዴት ነን? እውሸት በምድራችን ዙፋን ተክሎ ሲንጎራደድ የዕምነት አባቶች ምን ማለት ነው የሚጠበቅብን? ምርጥ ክራቫት አድርጎ አትሮኑ ላይ እየተጎማለሉ ፓስተር እገሌ እየተባሉ በስብከት ብልጠት የግል ዝናን ማስጠበቅ ነው እንዴ የዕምነት መሪ መሆን?። ወይስ መስቀል ጨብጦ፤ ጢምን አንዥርግጎና ረጅም ቀሚስ ለብሶ አባ መባል? ወዴት ነው እውነት ? ይህ ጥያቄአችን ከዕውነት ጋር ወግነው ዋጋ እየከፈሉ ያሉትን የዕምነት አባቶች አይመለከትም የመንፈስን ነገር ጥለው በስጋ ከገዳዬች ጋር ለተዛመዱት እንጅ!። ጀርመናዊው ፓስተር ደየትሪክ ቦንሆፈር  ለሂትለር ጥይት ደረቱን አሳልፎ የሰጠው አይሁዶች ለምን ይገደላሉ ? ሰው መግደል ኃጢአት ነው በማለቱ ነው። እንደኛው የሰማይም የምድርም አርበኛ እንደሆኑት እንደ  አቡነ ጴጥሮስ  ማለት ነው።

እያልን ያለነው ልክ እንደ ሙስሊም ወንድሞቻችን የህወሃት ሴራ ገብቶአችሁ ታገሉ፤ ለዕውነት ቁሙ፤  ለምትመሩት ህዝብ የዕውነት እረኝነታችሁን አሳዩ ነው። የስልጣኑን ወንበር ይዘው የሚዘርፉትን ፤ የዘር ማጽዳት ወንጀል የሚፈጽሙትን፤ ሃገር እየቆራረሱ የሚሸጡትን ህሊና ቢስ የሴኦል መልዕክተኞችን ፃ መንፈስ ርኩስ በሉልን ነው። ይህ የጨለማ ወቅት ያልፍና እንዳንተዛዘብ!። ዕውነተኞቹ የዕምነት መሪዎች ግን እንደ ንጉስ ኢዬሳፍጥ እናንተም የምትመሩትን ህዝብም በጾም የምትጠምዱበት ጊዜ ነው እንላለን።

ለተወደድከው የትግራይ ህዝብ፤  ወቅቱ ለሁላችንም አስተውለን የምንራመድበት ሃገርም እንደ ሃገር ህዝብም እንደ ህዝብ እንዲቀጥሉ የየድርሻችን የምንወጣበት እጅግ ወሳኝ ወቅት ላይ እንገኛለን።  በህወሃት ስም በበቀል የተደራጁት የባንዳ ልጆች ትላንትና ኢትዬጵያ የምትባል ሃገር እንድትኖረን ከጠላት ጋር የተዋደቁትን የአባቶችህን ታሪክ ለማደበስና የባዕዳን ጌቶቻቸውን የቆዬ ሃገርህንና ታሪክህን የማጥፋት ህልም ለማስፈጸም   አንተንም እንደሌባ መሸሸጊያ ዋሻ ለመጠቀም ሲል ብቻ ባቀደው ስውር የአጀንዳው ቀለበት ውስጥ እንድትገባ ተደርገሃል ይህንንም ስልት ለማስፈጸም ከቀሪው የኢትዬጵያ እህትና ወንድሞችህ መለየት አንዱ የውንብድና ዘዴው ነው  በዚህ መሰሪነቱም ቀን ከሌት እየሰራ ከወጥመዱ እንዳትላወስ ተደርገሃል ለዚህ እኩይ ገመድ መበጠሻው ስለት ደግሞ ከቀሪ የኢትዬጵያ ወንድሞችህ ጋር ማበር ነው ። የእንግዴ ልጅ ልትላቸው ይገባል።

እነዚህ የአንተ የሆነ ባህል፤ ዕምነት የሌላቸው ወሮበላ ወዲኒዎች በስምህ ከጉያህ ይውጡ እንጅ በየትኛውም መለኪያ ቢሆን አንተን ጨዋውንና እውነተኛውን የትግራይ ህዝብ ይወክላሉ ብለን አናምንም። ምንህ ይመስላቸዋል? አንተ የኢትዬጵያዊነት መሰረት ነህ እነርሱ ደግሞ ኢትዬጵያ የምትባል ሃገር የለችም የሚል ስብከት ነው ያላቸው ምክኒያቱም ኢትዬጵያ የምትባል ሃገር ከቀጠለች የዓድዋ ድል ሊታሰብ ነው፤ የእነምኒሊክ የነአሉላ የእነባልቻ የሌሎችም ጅግኖች ስም ሊታወስ ነው ይህ ደግሞ ለባንዳ ልጆችና ለጌቶቻቸው ስድብ ነው ውርደት ነው አንገት መድፋት ነው ስለዚህ የድል በዓሎቻቸን ሲከበሩ እንዳያዪ የጀግኖቻችን ስም ሲጠራ እንዳይሰሙ ኢትዬጵያ የምትባል ሃገር ትፍረስ ግልግል!። በዕምነት ነው የሚመስሉህ ? በጭራሽ! በዚህ በኩልማ  የእምነትህ መሰረት የሆነውን የኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን አከርካሪዋን ሰብረነዋል እያሉ በየአደባባዪ በሳጥናኤል መንፈስ እየፎከሩብን ነው። እነርሱ ስልጣን ላይ ስላሉ የድህነት ቀንበር ከላይህ ተሰብሮአል? ውሸት ነው  የሃገሪቱ ሃብት የሚንከባለለው በአንድ የዘር ትሥስር በመሰሪነት ቃልኪዳን በተጋመዱ የጨለማ ሰዎች መሃከል መሆኑን ሁሉም ኢትዬጵያዊ ያውቃል ። ምናቸው ነው የተረፈህ ከክፉ ስማቸው በቀር? እናም በቃችሁ ልትላቸው ይገባሃል።

ሰፊው የትግራይ ህዝብ ሆይ እመነን የአማራ ህዝብ ይወድሃል፤ የኦሮሞ ህዝብ ይወድሃል፤ ሱማሌው፤ ጉራጌው ሌላውም እንዲሁ ይወድሃል!። አዎ እንወድሃለን። ስማን! ከእነዚህ ወንበዴዎች መለየትህን ግን አውጅ!። ከወንድሞችህም ጋር ተባብረህ ቁም!። አሉላ ጀግናችን ነው፤ ዬሃንስ የእኛ መሪ ናቸው ሌላው ቀርቶ በኢትዬጵያዊነቱ ምክኒያት ብቻ ከህወሃት ባንዳዎች ተነጥሎ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ጀግናው ኃየሎ ም የእኛ ጀግና ነው። ከአዲሱ ትውልድ የፈለቁት እነ አብርሃ ደስታ የእኛ ጀግኖች ናቸው። እነ ገ/ መድህን አርአያ፤ ስዬ አብርሃ፤ ገብሩ አስራት እና ሌሎችም ወንድሞቻችን ህወሃት ለማንም የማይጠቅም ከሃዲ ቡድን መሆኑን እየመሰከሩ ከሌለው ኢትዬጵያዊው ወገናችው ጎን ከቆሙ ውለው አድረዋል የነዚህን ልጆችህን ምክር ስማ!።  በቅርቡ ም የትግራይ ልጆች ተሰባሰበው ያወጡት መግለጫ መልካም ጅምር ነውና አብረሃቸው ልትቆም ይገባሃል።

ድል ለኢትዬጵያ ሰፊ ህዝብ!!!

እግዚአብሄር ኢትዬጵያን ይባርክ

 

Posted on August 18, 2016, in Andinet, Andinet party, esat.com, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: