(ሰበር ዜና) – በጎንደር ለምን ነጭ በነጭ ለበሳችሁ በሚል የትግራይ ነጻ አውጪ አልሞ ተኳሽ በወሰደው እርምጃ 4 ሰዎች በጥይት ተገደሉ

August 20, 2016

በዛሬው እለት በጎንደር የአምባገነኑን መለስ ዜናዊን ሙት ዓመት አናከብርም ብለው ነጭ ልብስ በመልበሳቸው በአልሞ ተኳሾች ከተገደሉት 4 ሰወች አንደኛው::

በዛሬው እለት በጎንደር የአምባገነኑን መለስ ዜናዊን ሙት ዓመት አናከብርም ብለው ነጭ ልብስ በመልበሳቸው በአልሞ ተኳሾች ከተገደሉት 4 ሰወች አንደኛው::

(ዘ-ሐበሻ) በዛሬው እለት ጎንደር ከተማ የአቶ መለስ ዜናዊን ሙት ዓመት አናከብርም በሚል ለተቃውሞ ነጭ በነጭ ከለበሱት መካከል በአጋዚ ሰራዊት 4 ሰዎች በጥይት ተደብድበው ተገደሉ:: የአጋዚ ጥይት ሰለባ ከሆኑት መካከል አንዱ ወጣት ፎቶ በማሳት የሚተደደር ወጣት ግዛቸው የሚባል እንደሆነና ለምን ነጭ ልብስ ለበስክ በማለት ቀበሌ 03 አስተዳደር አካባቢ ከጓደኞቹ ነጥለው በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ደብድበው ከገደሉት በኋላ አስከሬኑን ወደ ጎንደር ሆስፒታል ወስደው ጥለውት ተገኝቷል ሲሉ ዘ-ሐበሻ ያነጋገረቻቸው የአይን እማኞች ገልጸዋል::

የጎንደር ወጣትም አስከሬኑን ከሆስፒታል በማስወጣት ወደ ከተማው ይዘውት በመዞር ላይ እንዳሉ ወታደሮች በአስለቃሽ ጢስ የወጣውን ወጣት በጢስ በመበትን አስከሬኑን ቀምተው በመንግስት መኪና በመጫን ወስደውታል፡፡ ይህ የተደረገው ዛሬ ነሀሴ 14 ቀን 2008 ዓ.ም ከስዓት በሀዋላ ነው::

ዘ-ሐበሻ ከስፍራው ያነጋገረቻቸው አንድ ሰው እንደገለጹልን “አሁን ጎንደር ከተማ ውስጥ የሚንቀሳቀስ ሰው የለም ወታደር ብቻ፡፡ ይህን መረጃ የምሰጣችሁ እኔም የድርሻየን እንደ ኢትዮጵያዊነት የተሰማኝ ትልቅ ሃዘን ሆዴ ውስጥ ነው የሚሰማኝ ፡፡” ብለውናል:

Posted on August 20, 2016, in AFRICAN NEWS, Andinet, Andinet party, esat.com, ETHIOPIA ENGLISH, Ginbot 7, OLF. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: