የሕዝብን አመጽ የሚያሸንፍ ኃይል የለም! (ይፍሩ ኃይሉ)

በይፍሩ ኃይሉ

በቅርቡ ”ጎንደር፤ እሳቱን በሣት ያጠፋ ጀግና ነው “ በሚል አረዕስት ባቀረብኩት ሐተታ ውስጥ የወልቃይት ጠገዴን የማነት ጥያቄ ተመርኩዤ ነበር። በዚያ ላይ የጎንደር ቁጣና ያስከተለው፤ ከአትናፍ እስከ አጥናፍ የተቀጣጥጠለ የሕዝብ በውልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ላይ ብቻ የተወሰነ ሣይሆን፤የመላው የኢትዮጵያን ሕዝብ የልብ ትረታንና ብሶት የነካ በዉድም ሆነ በግድ ወያኔ ከሥልጣን መውረድ አለበት የሚል ነው ። ከእንግዲህ የወያኔን የግፍ ቀንበር የምንሸከምበት ጫንካችን ትልጧልና ከትከሻችን በፍጥነት ይዉርድልን” እያለ ነው የሚጮኸው። ይህ ገና የመጀመሪያው “በቅቶኛልና የአዳምጠኝ” ጩኸት እንጂ ወያኔ የኢትዮጵያ ሕዝብ የደገሰለትን ያወቀው አይመስለኝም። እንደለመደው ያችኑ ያችን የከፋፍለህ ግዛ ዘዴውን እንዳይጠቀም ጎንደር ከኦሮሞው ከመራቁም በላቅይ ‘ የኦሮሞ ሕዝብ ስቃይ የኔም ስቃይ ነው፤ የኦሮሞ ደም ሲፈስ የኔ ደም እንደፈሰሰ እቆጥረዋለሁ “ እያለ ሰንደቁን አንግቦ ሲጮሕበት ወያኔ ወዴት ይሩጥ? ግን ያንኑ የፈረደበትን የትግራይን ሕዝብ ከማወናበድ አልጠቆጠበም። ጥቂት የአማራ ሆዳሞችና ለላንቲካ የተቀመጠው ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ፤”ወልቃይት የትግራይ አካል ለመሆኗ ታሪክ ይመስክራል..” እያሉ ማንዛረጥ ጀመሩ።የጎንደር ሕዝብና የኢትዮጵያ የታሪክ ምሁራን ከት ብለው ሳቁ አሁንም እየተንከተከቱ ነው። የወያኔ የቅርብ ወገኖቹና የቀድሞ ታጋዮቹ፤”የደም ዋጋህ ነው” እየተባለ፤ከድሃ እየተነጠቀ ዛሬ ባለቪላ፤ ባለብዙ መኪና፤ባለ ብዙ ኃብት፤አብሮ ከወያኔ ጋራ ወልቃይት ጥገዴም ላይ ሆነ በሥላን ሙጥኝ ማለት ለኔ ይገባኛል ቢል አይፈረደበትም። ከሃያ አምስት ዓመት በፊት ለግሩ ጫማ ያልነበረው፤ዛሬ የግሩ ጫማ ከጣሊያንና ከስፔይን፤ ከአሜሪካና ከእንግሊዝ የመጣ ነው። የዛሬ ሃያ አምስት ዓመት የወያኔ ተጋድይ፤ቁርሱን በልቶ ለምሳውና ለራት፤”ከየት ይመጣ ይሆን?” እያለ ሲጨነቅ የኖረ፤ዛሬ እምብርቱ እስኪገለበጥ በዚግኒና በጢብሲ፤በዶሮወጥና በምንቸት አብሽ ይቀበተታል። ጮማ እንደጎመን የቆርጣል።የኢትዮጵያ ድሃ በጠኔ ሲሰቃይ፤ ወያኔ በቁንጣን ሲፈራገጥ ያድራል። እንኳን ቀምሶት ሰምቶት ያማያውቀውን ዊስኪና ብራንዲ፤ሻምፔኝና ዉድ የወይን ጠጅ ይጎንጫል።ጢንቢራው እስክዞር ድርስ ሰክሮ፤ በየቡና ቤቱ ሽንቱን በሱሪው ላይ ያንዠቀዠቀ፤ ከኪሱ ሽጉጡን አውጥቶ በሰው መያል ጥይት ይተኩሳል። ጸጥታ አስከባሪው ጸጥታውን ያደፈርሳል። የዚህ ዓይነት ባለጌ ከዚህ  ከተንጠለጠለበት ኮርቻ በፈቃዱ ይወርዳል ማለት ዘበት ነው። “ዋይ!ከዚህ ወርጄ እንደገና አጸበለስ ለቀማ የምሄደው?” ነው የሚለው። ይህ የሚወገደው በግድ ገባር ግንብሩን እያሉ በማጋደም ብቻ ነው። ሚያሳዝነው፤ከማራው፤ ከኦሮሞውና ከሌላውም ብሔረሶቦች ተውጣተው፤ከወያኔ ጋራ ለግል ጥቅም ሲሉ ብቻ፤ወገኖቻቸውን ሲገድሉና ሲያስገድሉ፤ከወያኔ ጋራ አብረው ሲዘርፉ የኖሩ ባንዳዎች ዛሬ መሬ ተከፍታ ብትዉጣቸው ይሻላል። ቀኑ የመሸው ለወያኔ ብቻ አይደለም ለሱም ጭምር ነው። ዛሬ እነሱና ወያኔ የታሰፈሩበት መርከብ ይዙዝቸው ሊሰምጥ ከዉቂያኖስ ላይ እየዋለለ ነው።Revolt in Ethiopia

        የተነሳሁበት አረዕስት የሕዝብን አመጽ የሚያሸንፍ ኃይል የለም ብዬ ነው። ወያኔ እንደሚደነፋው ከሆነ ወያኔ ከሥልጣን ንቅንቅ አይልም የሚሉ እንደሚበዙ አውቃለሁ። ጎበዝ ይቻላል።ወያኔ ብረት ለበስ ፍጡር አይደለይ። እሱንም ጥይት ይበሳዋል፤ሳንጃ ይቀደዋል፤ዱላም ይፈረክሰዋል።እሱ የሚለን፡”እስከጥርሴ የታጠቅሁ፤ የሰለጠነ ወታደር ያለኝ፤የሃገሪቷን ቁልፍ ቁልፍ ቦታ ጨብጬ የያዝኩ፤ በመእራብ ሰሜን ወዳጄ፤ሱዳን ዋርዳያ ቆሞ ማንኛውም የኔን ተቀናቃኝ ጠላቴን፤ወደኔ አያሳልፍም። በሥራቅ ደቡብ ብሄድ ጂቡቲና ሱማሌ በቁጥጥሬ ስር ናቸው። በደቡብ ብሄድ እንደንዝርት የማሽከረክራት ኬንያ ከቃሌ አትወጣም። የመላ ኢትዮጵያ ሕዝብ ቢንጫጫ ባንድሙቀጫ አይደለምወይ?” ነው። በዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲያውን ሥራ በሚመለከት፤ የዘርፍኩትን ዶላር እያፈሰስኩ፤አሉ የተባሉ ሎቢይስቶችን እየቀጠርኩ አፋቸውን አዘጋቸዋለሁ። ደግሞሳ፤ በአይሲስ ሆነ በአልካይዳ ለሚነጰርጰሩ ሀገሮች፤ለአሜሪካም ሆነ ለአውሮፓ ያለኋቸው እኔ መሆኔን፤ በተለመደው በውሸት ፕሮፓጋንዳ ምን ያህል ከችግር ላይ እንደሆኑ፤በገዛ ሀገሬ ቦምብ አፈንድቼ፤ የሃገሬን ሕዝብ እየፈጀሁ፤የእሬሣ ክምር አሳያቸዋለሁ። ማነው ታዲያ እኔን ፍንክች የሚያደርገኝ፡” ባይ ነው። የሕዝብ እንባ ጠባቂዎች ጩኸት የት ሊደርስ? ይለናል። ዕዉነትም ይህንን ቱልቱላ ላጣጣመው ፈሪ ጥጥቅ ያስፍታል። ግን እኮ ጎበዝ ቅድመ አያቶቻችን አድዋ ሲዘምቱ፤የሰለጠነና እስከ ጥርሱ ድረስ የታጠቀ ወታደር አልነበራቸውም። “ሸፍነን፤ ድረስልን” የሚሉት ሱዳንም፤ ጂቡቲም፤ ሱማልያም አልነበሩም። ለሃያላን መንግሥታት የሚጮህበትን፤ዘዴውንም፤ መንገዱንም አያውቁትም ነበር። የነበራቸው ዕውነትኛ የሃገርና የወገን ፍቅር ነበር። የንበራቸው አንድነታቸውና መተማመናቸው፤ በይበልጥም የንበራቸው ወኔና ቆራጥነት ነበር። ዓለምን ያስደነቀው የአድዋ ድል የተገኘው በጦር መሣርያ ብልጫና በሰለጠነ የጦር ኃይል አልነበረም። በየአንዳንዱ ጀግና የደም ምሳሽና የአጥንቱ ክስካሽ የተገኘ ድል ነው።

       ወያኔ “እንኳን ለምሣ ለቁርስም አይበቁኝ” ያለ በሚደነፋው ከንቱ ወሬ አንደናገጥ። ወያኔ ምን ይሳነዋል?”ሽንታም አማራ ብሎም ሰድቦናል።ወያኔ ዛሬ የሚዋጋው ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋራ ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሞ ወዳጅነቱ እንጂ፤ጸቡ ለጠላቱ አይበጅም። ዛሬ በአስራ አንደኛው ሰአት፤ለሚገኝበት አጣብቂኝ ሁኔታ፤ ወያኔ፤ለሥልጣን ያበቃውን፤የነፍስ አባቱን የሻብያን መንግሥት እየከሰሰና እየወነጀለ ነው።እራስክ ቻል ወያኔ፤ ጸብህ ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋራ ነው። እነደዛር በሰው ላይ አትቆለል። አልሰማህም እንዴ?

“ይተኩሷል እንጂ  አዘልሎ ከጅ

እንደ ዛር ብሰው ላይ ቢደረቡ አይበጅ።” ሲባል? ወደድክም ጠላህም አሁን ሃያ አምስት ዓመት ሙሉ” እኔ በመጣሁበት መንገድ ኑና ሞክሩኝ!” እያልክ ስትፎክር ኖረህ ዛሬ ጀግናው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያን የምትወደውን የባሩድ ሽታና የጥይት ጩኸት ሊያጠግብህ ገና ትጥቁን እያስተካከለ እያለ መነው ፈጥነህ ቅሌን ጨርቄን አበዛሕ? ትላንት “የአማራና የኢትዮጵያን ኦርቶዶስ ቤተክርስቲያን የጀርባ አጥንት ሰብሬ አድቅቄዋለሁ እያልክ ስትደነፋ፤ ዛሬ እንዴት የኢዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ትዝ አለችህ? እንኳን ቄስ መነኩሴ፤ እንኩንስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲን ይቅሩና፤ተመልሰህ ከናትህ ማሕጸን ዉስጥ ብትገባ፤ በሰፈርክበት ቁና ልትሰፈር፤ የዘራኸውን ልታጭድ፤የግፍ ምርትህን ልትሰበስብ ቀኑ ስለደረሰ ከዚያ የሚያድንህ የለም። ከርስቶስ ዳግም ተመልሶ ወደዚች ዓልም መምጣቱ እነደማይቀር፤ያንተም በኢትይዮጵያ ሕዝብ ፊት ለፍርድ መቅረብህ አይቀሬ ነው። እንዴት? በለኝ።

       ታሪክ አንብበሃል ብዬ እገምታለሁ። በታሪክ ውስጥ በቀደምትነት ከሚገለጹት የሕዝብ አመጾች ዉስጥ፤የፈረንሳይ፤የአሜሪካኑ፤ የቻይናው፤ የቀድሞው ተ1917 የሶቬትና እንደዚሁም የሄሺያን፡(ሃይቲ) ሪቮሉሽን፤ ይጠቀሳሉ። እነዚህ ሁሉ አምጾች በጨቋኝ ገዢዎቻቸው ላይ ስለነበረ፤ያንን የበለጠና የታጠቀ ኃይል መቋቋም የሚችሉበት የወታደራዊ ብቃቱም፤የመሣሪያም ኃይል አልነበራቸውም። የነበራቸው፤ከታሰሩበት ሰንሰለትና ከተሸከሙት ቀንበር ለመላቀቅ በአንድነት በመተመመንና በቅራጥነት፤ የተከፈለው ዋጋ ከፍለው እራሳቸውን ነጻ ማውጣት ነበር። የሁሉም የታቀደውን ግብ መተው የሃገራቸውን የፖሊቲካ መልከአ ምድር ለውጠዋል።አሁን እንኳ በቅርቡ በሰሜን አፍሪካ፤በቱኒዚያ፤ሊቢያ፣ግብጽ የተከናወን ብናስታውስ ብዙም ሳንዛዛ እነዚህ ሶስት አገርች ብቻ ይበቁን ነበር። እኔ ግን እንደ ምሳሌ ወስጄ፤ ነጥቤንም ያጠናክርልኛል ብዬ ስለምገምት፤በ1975 ዓም የተደመደምውን የቪየትናን ጦርነት ነው። እንድሚታወቀው የአሜሪኪአን በጦርነቱ ዉስጥ ጣልቃ መግባት የጦርነቱን እድሜ ያሳጥረዋል ተብሎ ነበር። በርግጥም አሜሪካ ያለ የተባለውን የጦር ወታደሯን፤ በጥራቱን ሆነ ባይነቱ ወደር የማይገኝለትን የጦር መሳሪያ እያስጣጠቀች ላከች። ቆራጡ የቬትናም ሕዝብ የአሚረካንን የጦር አውሮፕላኖችንና ሄሉኮፐሮችን እንደቅጠል እያራገፉ ጣላቸው።፡ያን የሰለጠነ የጦር ወታደርም እንደዚሁ በራሱ መሳሪያ ቆሉት። ታላቂቷም አሜሪካ እጅ ወደላይ፤ በቃኝ በላ፤58000 ወታደር በላይ ሕይወቱን አጥቶ፤ስፍር ቁጥር የሌው ቁስለኛ ተሸክማ ወደአገሯ ተመለሰች። ይህ እንግዲህ የሕዝብ አመጽ የሚገታው ኃይል እንደሌለ ያሳያል።

      በጡት አባታችሁ በአሜሪካ ወዳጅነት ብዙም አትመኩ። አሜሪካ እኮ የአጼ ኃይለጽላሴም፤ ለኢራኑ ሻህም፤ ለግብጹም ሙባረክ ወዳጅ ነበረች። ግን፡በዚያች አስራ አንደኛዋ ሰአት ታላቂቷ አሚኤሪካ ለአጼ ኃይለሥላሴም፤ ለሻሁም፤ ለሙባረክም አልደረሰችም። ምናልባት ለነ እንዳተ ያሉ ጥላቢሶች አሜሪካ ግድ ይኖራታል ብላችሁ ታስባላችሁ? እግዚአብሔር ይመስገን የኛ አባቶች በራሳችን እንጂ፤በሌሎች መተማመንና መመካትን አላስተማሩንም። ለናንተ ግን ለፈረንጅ ጭራ መቁላት አዲስ ነገር ስለአልሆነ ምንም አይመስላችሁም። ደግሞሳ በልመና የተራቀቃችሁ አይደላችሁም እንዴ?እናንተ በሃያ አምስት ዓመት ዉጥ የቀፈፋችሁት፤(በልመና የቃረማችሁት፤) ከአጼ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት እስከ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም አስተዳደር ድረስ በርዳታ የተገኘውን እንደሚበልጥብ ይታወቃል። ልዩነቱ የቀድሞዎቹ መሪዎች በሕዝብ ስም ለምነው ያመጧትን ለሕዝብና ለሃገር ነው ያዋሏት።፡እናንተ ግን እራሳችሁን አደለባችሁበት።

       ከላይ ለማስረዳት እንደሞከርኩት የሕዝብ አመጽ በድል እንጂ በሽንፈት አይጠናቀቅም። የወያኔም ጸብ ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋራ ነው። ወያኔ በኢትዮጵያ ሃብት በልጽጎ፤ እስከ ጥርሱ ድረስ ታጥቆ፤በሃብታችን አለኝ የሚለውን ጦሩን አስታጥቆ፤ማንነታችንን ለውጦ ትግሬዎች ሊያደርገን፤ለም መሬታችንን ወስዶ የትግራይ ሊያደርግ ቆርጦ መነሳቱን ዛሬ፤ጸሃይ የሞቀው፤ ሰው ያወቀው ምስጢር ሆኗል።የመይሳው ሃገር ተቆርጦ ከትግራይ ጋር ሲጠቃለል፤ የወልቃይትን ሕዝብ  ትግሬ እንጂ አማራ አይደለህም  ሲባል፤ እንኳን ጎንደሬውን፤ ጉራጌውን ከመሃል ሸዋ፤ ወላይታውን ከጋሞጎፋ፤ሲዳማውን ከሲዳሞ፤ኦሮሞን ከያለበት ደሙን ያፈላዋል። መንዜውና መሬው፤ተጉለቴውና ሸንኮሬው በንዴት ቆሽቱ ያራል።እኔንም ይፋቴውን፤የወገኔ የጎንደር ሕዝብ በንቀትና በድፍረት የመይሳው ዘር ዓይኑ ሲጓጎጥ ስመለከት፤እንደ አሞራ በረህ፤አርማጭሆ ገብተህ እደር ይለኛል።አሁን በወገናችን ላይ፤ ከኦሮሞ፤እስካፋር፤ከአርባምንጭ እስድ እስከ ሲዳማ፤ በየለቱ የሚፈጸመውን ግፍ ሳስበውና ሳሰላስለው፤ አንዳንድ ጊዜ እንደሕልም ይመስልኛል። በዕዉነት እነዚህ ሰዎች ከትግራይ አብራክ የወጡ ኢትዮጵያውያን ናቸው ወይ? እያልኩ እራሴን እጠይቃለሁ። በጎንደር የሚደርሰውን ስቃይና መከራ ስመለከተው፤እራሴን ልስት ትንሽ ይቀረኛል። ደግነቱ ባለወኔው ያገሬ ልጅ በከተማ መሃል ጥይቱን እየዘራ፤ ወያኔ ዓይኑን አፍጥጦ እያየው፤ባጠገቡ እየፎከረ ሲሄድ ምንኛ ያኮራል። ትላንት “ሽንታም” የሰደበውን ዛሬ እሱ በሱሪው ላይ እያሸና፤ በክላሽ ጥይት እያርገበገበ እንደ ዝንጀሮ ሲያባርረው እየተመለከትን ነው። ይህ ጀግንነቱ፤እንደሰደድ እሳት በፍጥነት ወደ ሌሎችም አካባቢ እየደረሰ ነው።

የጎንደር አቀንቃኝ፡

“የጎንደርን ጀግና ከስቶ፤ ጠቁሮ ቢያየው፤
ትግሬው ጎንደሬውን ጅማት ስጠኝ አለው።
ወይ ዘመን ወይ ጊዜ ሁሉም ተለዋውጦ፤
ባንዳ አገር ይገዛል አርብርኛው ተቀምጦ።
ወያኔ ደፋር ነው ላፉም ለከት የለው፤
የጎንደርን ጀግና ትግሬ ካልሆንክ አለው።
ወይ ልክ አለማዋወቅ አወይ አደፋፈር፤
በሰፈርው ቁና እሱም ሳይሰፈር፤
አጭደን ሳንከምረው፤እንደ ግንብ ድንጋይ፤
የምን አስታራቂ የምንስ ገላጋይ፤
ሳናደራርበው አንዱን በሌው ላይ።”

እያለ ሲያቅራራ በኣይነ ሕሊናዬ ይታየኛል።፡ዱሮ በልጅነቴ አባቴና ጉደኞቹ የአርበኝነት ጀብዷቸውን እያንሱ፤ አዝማሪ ቆሞ ግጥም እየተነገረው፤ ጀግናው ሰዉዬ አባረህ በለው!! እያለ ግጥሙን ሲደረድር፡ የሸነጠው እየተንሣ ቤልጅግና ዲሞትፈሩን እየተኮሰ ሲፎክር፤ሳይ “አይ ምነው ያን ጊዜ ተወልጄ ቢሆን ኖሮ!” እያልኩ ባለመታደሌ አዝን ነበር።ዛሬ ከአርባ አምስት ኣመት በኋላ ያ እመኘው የነበረው ወንድነትን ማስመስከሪያ ጊዜ ሲመጣ፤ከጎራው ከ8000 ማይልስ በላይ እርቄ በቴሌቪዥን መስኮት ብቻ እመለውከተዋለሁ። በዚህ ወሳኝ ሰኣት ኢትዮጵያ ዉስጥ ሆኖ የናት አገሩንና የወገኑን ፍዳ መካፈል መቻል ምንኛ መታደል ነበር!!

ወያኔ እንደ ድንፋታህ በርግጥም፤የአገሪቷን የጦር መሣሪያ ጥርግርግ አድርገህ መቀሌ ላይ ቆልለሃል። በሕዝብ ሃብት አለኝ የምትለውን ጦር አሰልጥነሃል። ግን ይኸ ሁሉ ለኛ ምናችንም አይደለም። “የኢትዮጵያን (የደርግን ጦር አሸንፌ ነው ከዚህ የደረስኩት” እያልክም አትቀደድ:: የኢትዮጵያን ሕዝብ ከንድ አታውቀውም። በነጥርቅምቅሜ በደርግ መንግሥት ዉስጥ ዕውነተኛ የኢትይጵያ ጅግኖች፤አንተንም፤ጌታህንም ሻቢያን አምርተውህ; በኤርትራ በረሃ ላይ ወድቀዋል። የተረፈው የደርግ ጦር የምትለው ላንተና ለሻቢያ በሰላይነት የተሰገሰጉ ሆዳሞችና ሱሪይቸውን ያወለቁ አተላዎች ናቸው። አንተም፤ ጌታህም ሻቢያ እነዚህን ግርዶች፤በተቻለህ መጠን አኝከህ ሲበቃህ ተፋሃቸው። ይገርመሃል የድሮ ወዳጆችህ ያበላሹትን ለመጠገን ዛሬ በየአለበት ጎንበስ ቀና ሲሉ ይታያሉ። እንደላም እየነዳህ፤ እሱም መንገድ እየመራህ አዲስ አበባ ሰተት አድርጎ ያስገባህ የደርግ አገዛዝ ያንገፈገፈው፤መሞትም፤ መግደልም የሰለቸው ሠራዊት ነው። አንተ ግን ሕሊና ቢስ ባለጌ በመሆንህ የኢትዮጵያን ሠራዊት በአንድ ቀን ዠንበር በትነህ ከሜዳ ላይ አፈሰስከው። ታሪክ ይፋረድህ!!የኢትዮጵያ ሕዝብም መንገድ እመራ. ሲርብህ እያበላ፤ ሲጠማህ እያጠጣ፤ ሲመሽብህ እያሳደረ ነው ከዚህ ያደረሰህ። ለውለታው ምን ከፈልከው? እርሱበርሱ እያጋጨህ እንዲተላለቅ ሞከርክ፤ ቤቱን በቡልዶዘር በላዩ ላይ አፈርስክበት።እናት አገሩን ኢትዮጵያን ያለወድብ አስቀረህ፤ኤርትራን አስገነጠልክ፤ የሚኮራባትን ባንዲራውን ጨርቅ ብለህ ተሳደብክ። ትምክህተኛ አማራ ብለህ ሰደብከው። ዘረኛ በመሆንህ በዘርህ ተደራጅ አልከው። ቆራጡ አማራ በዘር መደራጀትን ላንተ ለዘረኛው ትቶ፤በኢትዮጵያዊነቱ ጸንቶ ይኸው ከዚህ ደርሷል።

ጸብህ ከዚህ ባለታሪክ ጀግና ሕዝብ ጋራ ነው። እንዳንተ በፈረንጅ ወዳጆቹ አይመካም፤አይመጻደቅም።

እንዳንተ ባለው የመሳሪያ ብልጫና ባሰለጠንከው ወታደር አይመካም። ሁለቱም የለውም። ግን በአስተሳሰቡና በሥነ ምግባሩ፤በሥነ ሥራቱ፤ በዲሲፕሊኑ ይበልጠሃል። ታንክና አውሮፕላን፤አዳፍኔና ባዙቃ የለውም። ግን አታስብ አንተ እያለህ እኛን የጦር መሣሪያ አይቸግረንም። አላማጣና ሊማሎሞ፤ደንገዜና ጣርማበር አድገን አንተን የምናጠፋበት መሣሪያ እንዴት ይቸግረናል። የጦር መሣሪያህንና ሠራዊትህን ጭነህ ስትንከረፈፍ በናዳ ብቻ ጭፍልቀን እንፈጅሃለን።”የናቁት ያስረግዛል” ሲሉ አልሰማህም? ያንተን 50 ካሊበር ማሽን ገን እኛ የጉንዴ ጥይት በአፈሙዙ እየከተትን ከጥቅም ውጪ እናደርገዋለን።

በይበልጥ ደግሞ ይህ የሰለጠነ ጦር አለኝ እያልክ ጉራ መንዛቱን አቁመው። ሠራዊቱ የኢትዮጵያ ሠራዊት ነው። ምናልባትም ይቺ መልክት ታትማ ለንባብ ከመብቃቷ በፊት፤ጀግናው የኢትዮጵያ ሠራዊት ባንተ በራስህ ላይ የክላሹን አፈሙዝ እንደሚያዞር አልጠራጠርም። እንደነከርኩህ አመጹ የሕዝብ አመጽ ነውና ሁሉም ይረባረብብሃል። በየአቅጣጫው እንገጥምሃለን።እንሞታለን፤ ግን ይዘንህ ነው የምንወድቀው። አስብ አንተ የኛ 6% ብቻ ነህ።6፡94 መሆናችን ነው።በለስ ቀንቶህ ከኛ 50%ቱን እንኳ ብትገድልና አንተም ጨርስህ ብትጠፋ፤አሁንም 44ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን እንተርፋለን። “ነብር አየኝ”በል፤ እንደነቀርሳ በሁለንተናህ ገብተን እንደ ገንደ ቆርቁር ከውስጥ ነው የምንቦጠቡጥህ። አልቆልሃል።አላማጣን ዘቅዘቅ አትላትም። ጀግናው ወለዬ ዘብ ቆሟል። በለስ ቀንትህ ደሴን ብታልፍ፤ ኮምቦልሻን አታላፋትም። ኣፍራታና ግድም፤ማጀቴና አንጾኪያ በተጠንቀቅ በሩን ዘግተው ይጠብቁሃል። ካራቆሬን ተዘቅዝቀህ፤መሃል ይፋትን ሰንጥቄ ጣርማበርን አልፋለሁ ማለት ዘበት ነው። ከዚያ ግባተ መሬትህ ይፈጸማል።ያደፈጠውን የይፋትን ነብር፤ አድብቶ የሚጠብቀውን የመሬን አንበሳ፤የመንዝን፤ የትጉለትና ቡልጋን ግሥላ ከጭኝቅላትህ እንዳይጠፋ።የመንጃርና የጅሩ፤የሸንኮራ፤ የየረርና ከረዩ ንስር አሞራ፤በቤልጅግ ጥይት ያንጠለጥልሃል። በአፋር በኩል አታስበው፤ እነሞት አይፈሬ አዘቦና እራያ የጥይት እራት ነው የሚያደርጉህ። ወደ አፋር ምድር ዘቅዘቅ በትል፤ እንደተርብ እየነደፈ፤የአሞሌ ጨው ቆፋሪ ነው የሚያደርግህ። ተሳክቶልህ በአዋሽ አቋርጠህ በኦሮሞ መሃል ለማለፍ ብትሞክር ጀግናው ኦሮሞ እያመረተ የጅግብ እራት ነው የሚሰጥህ።

ግን ክዚህ ሁሉ፤ “ኧረ ወዴት እየሄድኩ ነው?” ብለህ እራስህን ጠይቅ። አቅጣጫህ ስለሚያስፈራ፤መድረሻህም የባሰ ስለሆነ ከሕዝብ ታረቅ። ኢትዮጵያንና ሕዝቧን” ማሩኝ!” ብለህ ከዕግራቸው ላይ ወድቀህ ተማጸን። ቄስ መንኩሴ፤ሼህና ሃጂ አያስፈልጉህም። ከቤትህ ጀምር። የትግራይን ሕዝብ ይቅርታ ጠይቅ። የትግራይ መኳንንቶችና አዛውንቶች በቀጥታ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋራ፤በተለመደው ጨዋነትና የአገር ባሕልና ወግ፤ ቁጭ ብለው፤ሃያ አምስት ዓመት ሙሉ የተበተብከውን ዉሉ የጠፋበት ገመድ ፈተው፤ ሃያ አምስት ኣመት ሙሉ የአጨማለከውን የፖሊቲካ ቡኮ፤ መልክ አሲዘው፤ጊዚያዊ መንግሥት አቋቁመው፤አንተንም እንደንጨት ነድህ አመድ ከመህ፤ ኢትዮጵያንም በራሷ ላይ ከሚያንዣብበው የጥፋትና የሞት ጥላ ያድኗታል። መፍትሔው ይኸ ብቻ ነው። ይህን ባትቀበል፤ከምላሴ ጸጉር ንቀል እነደ ጢስ ብን ብለህ ትጠፋለህ።

በመጨረሻም የምነግርህ መርዶ አለኝ። “በሳለፍኩት ሃያ አምስት ዓመታት ዉስጥ የአከማቸህትን ዶላርና ወርቅ፤ብርና አልማዝ፤ ይዤ ወጥቼ፤አሜርካ፤ አውሮፓ፤ ኤዢያ፤ደቡብ ምሥራቅ እስያ፤ የትም ፤የትም ሄጄ ተደብቄ እየተደላቀቅሁ፤ ልጆቼን እያስተማርኩ እኖራለሁ።” የሚለውን ሕልምንህን አቁመው። እኛ ኢትዮጵያውያን፤ እንድሜ ለድርግ መንግሥትና ለናንተ ለአውሬዎቹ፤እኛ የሌንበት አገር የለም። የትም ሂድ የት፤ ስምህን ቀርቶ ጾታህን እየለወጥህ ለመሮር አትከጅለው። ከገባህበት እየገባን፤እንደ ከርከሮ ግልገል ከተደበቅህበት ጉድጓድ ዉእጥ እየጎተትን አውጥተን፤ለፍርድ፤በኢትዮጵያ ሕዝብ በፊት እናቆምሃለን። ያ ባለረእዩ ጌታህ መለስ ዜናዊ በድንጋጤ ክው ብሎ በደህና ቀን አረፈላችሁ። ያ የእንጨት ሽበት አቦይ ስብሃትም፤ ዛሬ የተወለደበትን ቀን እየረገመ ይግኛል። ኧረ ለመሆኑ በረከት ሰሞንን ምን አምጣ ብላችሁ ነው ጎንደር የላካችሁት? በረከት ትግሬም፤ አማራም አይደለም፤ጎንደር ተወልዶ ያደገ የኤርትራ የውሻ ቡችላ ነው። ያነእለት ከጎንደር በሕይወት በመመለሱ በጣም ተናድጃለሁ። አንዲት ጥይት የሚያጣብቅበት  አንድ ጀግና እንዴት ጠፋ?በሌላ በኩል ደግሞ ለንደሱ ዓይነት ወደል አህያ ዕረፍት ነው። ወይ ነዶ እኔና እሱ ኢትዮጵያ በርሃ ውስጥ ብንገናኝ፤ ጥይት ሳልተኩስ በቤልጂግ ሰድፍ መንጋጋውን አላቅቅለት ነበር። ግን ግድ የለም፤ የሁልችሁም ቀን ቀርቧል። አብራችሁ እንደመጣችሁ፤አብራችሁ አገር እንዳጠፋችሁ፤አብራችሁ የኢትዮጵያን ሕዝብ እንዳሰቃያችሁ፤ አብራችሁ የሃገር ሃብት እንድዘረፋችሁ፤በፍር ቀን ደግሞ፤እንደዚሁ እንዳማረባችሁ፤ኢትዮጵያን ሕዝብ ፊትለፊት ተጋፍጣችሁ፤ለሚጠይቃችሁ ጥያቄ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ፤ቀጥተኛውን መልስ እንድትሰጡት፤በሃገሪቱና በሕዝቧ ላይ፤ የፈጸማችሁት ወንጀልና የግፍ ድርብ፤ ያስገድዳችኋል። ያነእለት እናንተን አያድርገኝ።

ሞት ለወያኔና  ለሆዳም ባንዳዎች!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

ኢትዮጵያ በነጻነቷ ለዘለዓልም ትኑር!

– See more at: http://ecadforum.com/Amharic/archives/16825/#sthash.30eqx3Gl.dpuf

Posted on August 20, 2016, in Andinet, Andinet party, esat.com, Ginbot 7, OLF, oromo. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: