አዲስ አበባዎች ይነቅላሉ (ዳዊት ዳባ)

ዳዊት ዳባ

የሌሊሳ ተግባር ጀግንነት ነው። ድረጊቱ ትግሉ ላይ ያስገኘው ጠቀሜታ እስካሁን ከተባለለትም የላቀ ነው። ደስታዬንና ምስጋናዬን ለመገለፅ ቃላት የለኝም ። የኢሳት የእስፖርት ጋዜጠኛ ወንድማገኘው እንዲሁ ምስጋና ይገባሀል። ከአምት በፊት ያን ዝግጅትህን ሳዳምጥ እጅግ አድርጌ መውደድ ብቻ ሳይሆን አንድ ቀን የወንድም ሌሊሳ አይነት ጀግንነት እንደሚሆን ቀድሜ አይቼበታለው። ሰውዝ አፍሪካ ላይ የአለም ዋንጫ ሲደረግ መልካም አጋጣሚ ነበር። “እነሱም እኛም እስፖርቱን ለፖለቲካ {ለኛ ለትግል} ላንጠቀምበት ተስማማን “ የሚለውን ስሰማ አንጀቴ ነበር የተቃጠለው። በዚህ አይነት አስከፊ ጭቆናና ዘግናኝ አድሎ ውስጥ እየኖረ “ወገኛ ህዝብ” ብዬ ሁሉ በሆዴ ተሳድባያለው። እስፖርትና ትግል ስል መጎልጎል የጀመርኩት ያኔውኑ ነበር። በዚህ ጊዜ ነበር የጥቁር አሜሪካኖቹን ታሪክና ሌሎች ከእስፖርት ጋር የተገናኙ የትግል ታሪኮችን ያወኩት። ልፅፍበት እያሰብኩ ሳለው ዝግጅትህን አዳመጥኩ ድንቅ ሆኖ ስላገኘሁት በጭራሽ ልንበዛበዝበት አልፈለኩም። ሌሊሳ ያን ዝግጅት መስማት አለመስማቱን የማውቀው ነገር የለም። ጠቃሚ ሀሳብ እንዲሰማና ጉልበት እንዲኖረው ተደርጎ ሲለቀቅ ግን ጊዜ ይወስድ እንደው እንጂ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ብዙ እርቀት እንደሚጓዝ አውቃለው። ኢትዬጵያዊያን በዚህ አይነት ታላቅ መድረክ ላይ ባይሆንም ያደርጉት ጀማምረዋል። አሁንም ፈተናን በማውጣት የአገዛዙን የማስተዳደር አቅም ማዳከምና የማሳጣት ትግል ተደርጓል። እዚህ ትግል ላይ ከፍ ብሎ የሞራል ጥያቄ ተነስቷል። በፈለገ አይነት የከፋ ጭቆናና እየተጨፈጨፈ ቢሆንም ዜጋው ሲታገል ሊተላለፍ ስለማይገባው መስመር ሁሉ ተስብከናል። የሰው ልጅ ለነፃነቱና እራሱን ከጥቃት ለመከላከል የሚያደርገው የትኛው ተግባሩ ነው ትክክል የማይሆነው? የሚለው ጥያቄ በአይምሮዬ እንደተመላለሰ እንደከነከነኝ አለ።Ethiopia's Olympic marathon silver medallist Feyisa Lilesa seek asylum.

አንድ ባለንጀራዬ ትግሉ አንቀሳቃሾች ውስጥ ቅርብ ነው ብሎ ባሰበው ወንድም በኩል ይህን የውጪ ሜዲያዎች ዝምታ አስገድደን ልንሰብረው እንችላለን ሲል አዲስ ሀሳብ ለማስረፅ መክሮ ነበር። እኔ አለው አንድ አስር ሀያ ቆራጥ ታጋዬች ካሉ እናፈላልግና በቀጣይ ሰልፍ ስንወጣ ጋዝ ወይ ምላጭ ነገር ይዘን እንውጣ። በተገቢው ካልተስተናገድንና እውነታችን እስካልተነገረ ሌላ መጉዳት አይሆንልንም እራሳችንን ግን እንጎዳለን ብለን አዋራ እናስነሳ ሲል። አክቲቪስቱ አፍጥጦ እንደ እብድ ሲያየው ቆይቶ ምን ይበል ጥሩ ሀሳብ አለ እየተገረመ። ግን ተግባራዊ አልሆነም። እስከዛሬም ማሰብና መፈተግበር እንጂ የማይሰበር ነገር ግን የለም። ጀግናው ሌሊሳ ሰባበረው።

አዲስ አበባ ላይ በቅርብ ታላቅ ህዘባዊ እንቢተኛነት ይካሄዳል። የጎንደርና የጎጃም ህዘብ ላይ ጦርነት አውጀው ፍጅት እየፈፀሙ ነው። ይህንን ዝም ብለን ልናየው የሚገባ አይደለም። ህዝባዊ አመፁ እንደሰደድ እሳት አገሩን እያዳረሰና እየተጠጋ ቢሆንም ለጊዜው ለብቻቸው ተጠቂ የሆኑት በአገር አቀፍ ደረጃ ህዘባዊ እንቢተኛነቱን ማምጣት ስላልቻልን ነው። ከሳምንት በፊት አዲስ አባባ የነበረው ጥሪ ትክክለኛ እርምጃ ነበር። ይህ ሙከራ አገዛዙን ብዙ ሚሊዬን ብር እንዳስወጣው ሰማው። ታዲያ በየሳምንቱ እሁድ እሁድ አደባባይ እየወጣን ህዘባዊ እንቢተኛነት የምናደርግብት ቀን አድርገን ብንይዘው ስንት ሳምንታት ይህን ያህል ብር እያወጣ ሊዘልቅ ነው?። በነገራችን ላይ ያልተካሄደው አገሩን ወታደር በወታደር ስላደረጉ በጭራሽ አይደለም። እሱን ሌላ ቦታ ሰባብረውት እየወጡ እንዳለው በገፍ ወጥቶ መና ማስቀረት ይቻላል። እንዲሁም እንደ አዲስ አበባዊነቴ ስለዚህ ህዘብ እንቢተኛነቱን በተመለከተ የሚሰጡ ፖለቲካዊ ትንታኔዎች የበዙት የሚገዙኝ ሆነው አላገኘሗቸውም። ትግሉ ከኦሮሚያ ሊሻገር አልቻለም፤ እራሱኑ ህዝባዊ እንቢተኛነቱን በተመለከተም ሲሰጡ የነበሩ ትንታኔዎች ሁሉ ትክክለኛ እልዳልነበሩ እያየን ነው። ባለፈው ጥሪ ተቃውሞው ያለተደረገበትን ምክንያት ብዙዎች በስሱ ስለሄዱበትና ስለማይፈይድ እዚህ አላነሳውም። ትምህርት ሊወሰድበት ግን ይገባል። ያም ሆኖ ጥሪው ጊዜን ቦታና ሁኔታዎችን በአግባቡ የሰላ ነበር። መልክቶቹ ይዘታቸውና አቀራረባቸው ድንቅ ነበር። ላሁኑ ተደረገ አልተደረገ አይደለም ዋናው ነገር፡፤ መነጋገርያ መሆኑ በራሱ በቅርብ በቀጣይ ለታቀደው እጅጉኑ አጋዥ ነው።

ሰዎቻችን ዛሬም ግድያ መፍትሄ ነው ላይ ናቸው። ምንም አይነት የአንባገነን የሀይል ከህዘብ ሀይል አይበልጥም የሚባለው ዝም ብሎ መስሏቸዋል። ተመልከቱ ሌሊሳ ብቻውን ባፍጢም ነው አፈር ውስጥ የደፋቀው። ገና ገና ነው። ህዝብ መምዘዝ የሚችለውን ልምጭ በጣም በጥቂቱ ነው የተጠቀመው። የአዲስ አበባ ህዘብ ወደ ስድስት ሚሊዬን የሚጠጋ ነው። እራሱ አይደለም መኪና ቢያሰለፍ ፍፃሜ ይሆናል። ታክሲዎች ስራ ሲያቆሙ መኪናዎቻቸውን እቤት የማቆም ግዴታ የለባቸውም። እንደጎንደርና ጎጃም ህዘብ እቤቱ ቢቀመጥ አለተፈለጋችሁምና ጎሽ ውረዱን በአለም ዘንድ ይናኛል። ህዘብ ባንድ ጊዜ አንድን ነገር ማድረግ አይችልም ከሆነ ዛሬም ክርክሩ የኦሮሞን የጎጃምና የጎንደርን ህዝብ አይቶ መማር ለሚፈልግ ከበቂ በላይ ነው። ስድስት ሚሊዮን ህዘብ ስልክ አንስቶ ቢደውል ወታደሩን ሁሉ ይደርሳል። የዛኑ ቀን መሳርያ ያዞራል። ቀን ወስኖ ተቃዋሚዎች ቢሮ በመሄድ አባል ለመሆን ቢሰለፍ እረሱን የቻለ ታላቅ ሰልፍ ይሆናል። ላስር ደቂቃ በያለበት ቢቆም ቢጨፍር ቢስቅ ችግር ነው። ገንዘቡን መከልከልና ገንዘቡን በጁ ማድረግ ይችላል። እናንተም ልጆቻችሁም ንብረታችሁም የበዛው እዛው ነው ያለው። እራሱን ለመከላከል እነዚህን ገነሮች መያዣ ሊያደርጋቸው ይችላል። ከወሰነ ወሮ ሊቀማቸው የሚቺሉ ብዙ ወሳኝ የቀበሌ ቢሮዎች አጠገቡ አሉ፡፤ አንድ አይነት መልእክት የያዘ ወረቀት ቢለጥፍ አጥርና ስልክእንጨቱ ሁሉ በመልክት ያሸበረቅል። እየተመናመነ ባለ ሀይል ማፅዳቱ ብቻ ወራቶች ይፈልጋል። በዛ ላይ የሚለቅመው መሳርያ የያዘውን ካድሬ ነው።

አንድ ቀን ጠዋት ላይ ስትነሱ መንገዶች በሙሉ በከተሜው ህዘብ ተሞልቶ ሊገኝ ይችላል፤ አዲስ አባባ ለሚገኙ ቻይናዊያን በሙሉ ለቃችሁ ውጡ ብሉ ድብዳቤ ቢልክላቸውስ፣… ተዘርዝሮ አያልቅም።

አዲስ አበባ ላይ ለውጥን ፈላጊውም ሊያንቀሳቅስ የሚችለውም ህዘብ ቁጥር የበዛ ነው። የስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን በሚሊዬን አደባባዩችን ተቆጣጥረውት የነበረው ትናንትና ነው። ህዝቡ መታገል ሳይደክመው መሪነቱን በአደራ የተረከቡ መምራት ደክሟቸው ነው ትግሉ የቀዘቀዘው። ሶስት ቀላል የመብት ጥያቄዎቻቸው ውስጥ አንዳቸውም አልተመለሱም። ሳይገባቸው ለመከራ የተዳረጉ ንፁሀን ዜጎች ሂወት ጉዳይ ለሁላችንም የእግር እሳት ነው። ይህ የህብረተሰብ ክፍል የተደረጃና፤ ዘመኑ ባፈራቸው መገናኛዎች የተጣመረ ነው። ስራውን ያውቀዋል። የአዲስ አበባ ካድሬዎች ከሌሎች ክልሎች ላይ ካየነው ወግንታዊነት በላይ ከህዘብቸው ጎን ለመቆም ብዙ ተጨማሪ ምክንያቶችም አሏቸው። ትናንትና በመድረክ፤ በሰማያዊ፤ በአንድነት፤ በመኢአድ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የወጣው ህዘብ ሁሉ ዛሬ በተራው ትግሉን አንቀሳቃሽ ነው። የማቀናጀት ድክምት ካልሆነ የሚጠብቃቸውን እያወቁ አዲስ አበባ ላይ በቆራጥነት የተሰለፉ የኦሮሞ ወጣቶች ብዙውን መሬት ላይ የሚያስፈልገውን ስራ ይሸፍኑታል። የጎንደር ህብረት የዚህን ያህል ካንቀሳቀሰ በውጪ ያሉ የካሳንቺስ፤ የጎላ፤ የሽሮ ሜዳ… ማህበሮች ምስር ወጥ በሄንከን እየበሉ መበተን ብቻ ሳይሆን እራሳቸወን ወደ ለውጥ አንቀሳቃሽንት ይቀይራሉ። እንደሚታወቀው አገዛዙ ሁሌም ቆረጣ ነው። በከተማዋ ያሉ ማህበራት በተመለከተ መሪዎቻቸው ላይ ነው የሰራው። የሚያሞዳምደውም ። ሊገባቸው ያልቻለው አስተማሪውም፤ ታክሲ ነጂውም፤ ጋዜጠኛውም፤ ጥቃቅኑም… ያው ተራ ህዘብ ነው። ተራ የከተማዋ በለቤት ነው። የነዚህ ማህበራት መሪዎች ወና ስራ የህዘብን ትግል ለማውገዝ መሆኑን አባላቱም ህዝብም የለመደው ነው። በዋናነት አየሩ በለውጥ ሽታ ከታወደ በሗላ ምርጥ ጓደኛሞች በሙሉ አንዳንድ ሴል ናችሁ። በመቶ ሺ ሰሎች አዲስ አባባ ውስጥ አሉ ማለት ነው። ለአዲስ አበባዊያን ከድጋሚ ጥሪ በፊት በንቃት ሁኔታዎችን መከታተል፤ መወያየት እራስን ማዘጋጀት ሲታትሩ መጠበቅ ነው። ይተገበራል!!!።

ብሔራዊ ጭቆና ይብቃ።

– See more at: http://ecadforum.com/Amharic/archives/16857/#sthash.Xi4TJNWK.dpuf

Posted on August 30, 2016, in Andinet, Andinet party, esat.com, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: