ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ሰሞኑን በተደጋጋሚ እንደዛተው የአማራን ክልል የጦርነት ቀጠና አደርጋለሁ ብሎ ተግባራዊ አድርጓል። ንጹሃን የአማራ ተወላጆችን ህጻናትን ጨምሮ ያለርህራሄ ባሰማራው አጋዚ ታጣቂዎች እያስገደለ ይገኛል።የሕዝባዊ ወያኔ መሪዎች የአጋዚ ጦር ብቻ ሳይሆን በሀሰት የገበሬ ታጣቂዎችን ጭምር <<አባይ እንዳይገደብ የሚፈልጉ የሻዕቢያና የኤርትራ ተላላኪዎች ናቸው>> በሚል ወገን ወገኑ ላይ እንዲተኩስ አበል እየከፈሉ መሳሪያ እያስታጠቁ ጭምር አሰማርተዋል። ይሄ ብዙ ርቀት አይወስዳቸውም።ሐቁን የአማራ ምሊሻ ይረዳል።ያውቃል።ሕወሓት በአማራ ሕዝብ ላይ ወልቃይት የአማራ ነው በማለቱ ለሰላማዊ ተቃውሞ የሰጠው የጥይት ምላሽ ሰጥቷል። (more…)
Monthly Archives: September 2016
ከሰሜን ጎንደር የአማራ ሕዝብ ትግል አስተባባሪዎች ለምሊሻ ታጣቂዎችና ለመላው የአማራ ሕዝብና ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያዊ ወገናችን ሁሉ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ
በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት 20 እስረኞች መገደላቸው ተሰማ | ቃጠሎውን የሚያሳይ አጭር ቪዲዮ ይዘናል
(ዘ-ሐበሻ) በዛሬው ዕለት በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት የተነሳውን የ እሳት ቃጠሎ ተከትሎ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ 20 እስረኞች መገደላቸው ተሰማ:: በቅሊንጦ እስር ቤት አንጋፋ ፖለቲከኞች እና የሃይማኖት መሪዎች የታሰሩ ሲሆን የሟቾች ማንነት እስካሁን እንዳልተለየ ከአካባቢው የመጡ መረጃዎች አስታውቀዋል::
በሃገር ቤት የሚታተመው አዲስ ፎርቹን ጋዜጣም 20 ሰዎች ስለመገደላቸው የዘገበ ሲሆን 3 የ እሳት አደጋ ሰራተኞች ቆስለው ሃኪም ቤት ገብተዋል ብሏል:: (more…)
የኦሮሞው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ለምን ገብ አለ? | ጥበቡ ታዬ
አንድ የሕዝብ እንቅስቃሴ ለመነሳት ምክንያት አለው፣ለመቆምም እንዲሁ።ብሶትና ምሬት የሕዝብን እምቢባይነት ይቀሰቅሳል።እንቅስቃሴው ከተሳካ በድል ይጠናቀቃል፤ አለዚያም በመንግሥት ሃይል የጥቃት እርምጃ ለጊዜው ሊገታ ይችላል። በዚህ መልክ የሚረጋገጥ የበላይነት ቂምን ስለሚወልድ ቅራኔውና ትግሉ እስከነአካቴው አይጠፋም።ጊዜ ጠብቆ ያገረሻል።ሌላው ምክንያት ደግሞ በመንግሥትና በተነሳው ሕዝብ መካከል ውይይት ተካሂዶ ሕዝቡ የሚፈልገውን እንደሚያገኝ የተስፋ ቃል ተሰጥቶትና ያንን ተቀብሎ ከተነሳበት እንዲያፈገፍግ የሚያደርግ ስራም ከተሰራ የሕዝብን ትግል ሊገታው ይችላል። (more…)
አዲስ አበባ ውስጥ በቤት ውስጥ በመቀመጥ መንግስትንየመቃወም ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን የሃይማኖት አባቶች ለመንግስት ገለጹ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት አሥራ አምስት ቀናት መንግስት ከወትሮ በተለየ ሁኔታ በማዘጋጃ፣ በክፍለ ከተሞችና በወረዳወች የእያንዳንዱን ሃይማኖት ቤተ አምልኮ መሪዎችን በመሰብሰብ ውይይት ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡
የሕግ ባለሙያዎች ታሪክና ግዜ የጣሉባችሁን ኃላፊነት እንደምትወጡ ይጠበቃል! [በላይነህ አባተ]
በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
ታሪክና ግዜ በትውልድ ኃላፊነትን ይጥላል፡፡ ይህ ትውልድ በሮማውያን ዘመን ኃላፊነቱን በሚገባ እንደተወጣው ትውልድ ታሪክና ግዜ ኃላፊነት ጥለውበታል፡፡የሮማውያንን ተደጋጋሚ ጪፍጨፋ አያት ቅደመ-አያቶቻችን በሚያስደንቅ ጀብዱ መክተውታል፡፡ ከሮማውያን ቅኝ ገዥዎች ጪፍጨፋ በከፋ ሁኔታ በእጅ አዙር ቅኝ ገዥ አገልጋዮች ህጻናት ጭንቅላታቸውን በላውንቸር እንደሚበረቀሱ፣ እግራቸውን በባሩድ እንደሚቆረጡና ሆዳቸውን እንደሚዘረገፉ አምባ ጊዮርጊስ በዚች ቅጽበት አስገንዝቦናል፡፡ እነዚህን የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ አገልጋይ ጨፍጫፊ ባንዳዎችም ሕዝብ ግብግብ ገጥሟቸው ይገኛል፡፡ ይህ የጪፍጨፋ ግዜ ከገዳዮች የወገነውን እርጉሞችና ድምጣችንን አጥፍተን እንጀራችንን የምናሳድደውን አድርባዮች በትዝብት ቴሌስኮፕ ይመለከተናል፡፡ (more…)
አምባ ጊዮርጊስና ደብረታቦር በሁለት ቀናት ከ50 በላይ አማሮች ተገደሉ | በጎንደር የተደረገው ስብሰባ ያለውጤት ተበተነ | በደብረ ታቦር ዳግመኛ የቤት ውስጥ አድማ ተጠራ
የጠ/ሚውን አዋጅ ተከትሎ በመተማ፣ አምባ ጊዎርጊስና ደብረ ታቦር ከ50 በላይ ዐማሮች በሁለት ብቻ ቀናት ተገድለዋል
• በሽንፋ ከተማ የቀን ሠራተኞች በጥይት ተደብድበዋል
• በደብረ ታቦር ዳግመኛ የቤት ውስጥ አድማ ተጠራ
• በላሊባላ በግፍ ለተጨፈጨፉ ዐማሮች ጸለት ተደረገላቸው
• በጎንደር የተደረገው ስብሰባ ያለውጤት ተበትኗል (more…)
የኢትዮጵያ ነብሮች ሲበሳጩ ያጉረመርማሉ! (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ አሜሪካውያን የጀግንነት በላይነት የላቸውም፣ ማለትም የኦሎምፒክ ጀግንነት ጠቅላይነት፡፡ እ.ኤ.አ ነሐሴ 21/2016 የ26 ዓመቱ የኢትዮጵያ የረዥም ርቀት ማራቶን ሯጩ ፈይሳ ሌሊሳ በአንድ ወቅት በኦሎምፒክ ጨዋታዎች ታሪክ “የኦሎምፒክ ጨዋታዎች የፖለቲካ እንቅስቃሴ መግለጫ መድረኮች ሊሆኑ አይችሉም” በማለት ይገለጽ የነበረውን ሕግ ወደ ጎን አሽቀንጥሮ በመጣል በሪዮ ኦሎምፒክ ውድድር አስደናቂ የሆነ ታሪካዊ ድርጊትን ደግሟል፡፡ እ.ኤ.አ ጥቅምት 16/1968 በሜክሲኮ ኦሎምፒክ ተደርጎ በነበረው የ200 ሜትር የአጭር ርቀት የሩጫ ውድድር ቶሚ ስሚዝ እና ጆን ካርሎስ የወርቅ እና የብር ሜዳሊያ አሸናፊዎች ሆነው ነበር፡፡ በሜዳሊያ አሰጣጥ ስነስርዓት መድረኩ ላይ አድርገውት የነበረው ታሪካዊ ድርጊት በአሁኑ ጊዜ ትልቅ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ይገኛል፡፡ የእጆቻቸውን ቡጢዎች ከፍ አድርገው ከራሳቸውበ በላይ ወደ ላይ በማንሳት የጥቁር ሕዝቦችን አይበገሬነት ምልክትነት በይፋ አሳይተዋል፡፡ ፈይሳ ከውድድሩ ማጠናቀቂያ መስመር ላይ ሲደርስ ሁለቱንም እጆቹን አጣምሮ ከእራሱ በላይ ከፍ አድርጎ በማንሳት የኢትዮጵያን ወጣቶች የአይበገሬነት የኃይል ምልክት እንቅስቃሴ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በይፋ አሳይቷል፡፡ (more…)
ኢትዮጵያ፡ ከተቃውሞ እና ከተጋድሎ በኋላ!? (የአቶ ኦባንግ ሜቶ ንግግር በዋሽንግተን ዲሲ) – See more at: http://ecadforum.com/Amharic/archives/16871/#sthash.KgtIgRNj.dpuf
ኦባንግ ሜቶ
አሰላሙ አሌይኩም፣ እንደምን አላችሁ፣ አካም ጂርቱ፣ እንደምን አረፈዳችሁ (good afternoon everyone፡፡ የኢትዮጵውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ኅብረት በዚህ ስብሰባ ላይ እንድናገር ስለ ጋበዘኝ ልባዊ ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ፡፡
ከእናንተ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ጋር በመሆን ስለምትወዷት አገራችን የወደፊት ሁኔታ ለመወያየት መብቃት ታላቅ ዕድል ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት አገራችን በከባድ ቀውስ ውስጥ እንደምትገኝ ሁላችንም የምናውቀው ሃቅ ነው፤ (more…)
ይድረስ ለታጋዩ ሕዝባችን (1) — ፍርዱ ዘገዬ (ከአዲስ አበባ)
ፍርዱ ዘገዬ (ከአዲስ አበባ)
አንደኛ – የማንም ንብረት ቢሆን በተያዘው የሕዝባዊ እምቢተኝነት ሰበብ ማቃጠሉና ማውደሙ ጠቃሚም ተገቢም አይደለም – መራራው የትግል ጉዟችን ብዙ ማስተዋልና ብዙ ማሰላሰል ያለበት ይሁን፡፡ በርግጥ በእስካሁኑ ሁኔታ የዐማራው ትግል ብስለትና ጨዋነት የተሞላበት መሆኑና ልዩ ጥንቃቄ መደረጉ የሚያስመሰግን ነው፡፡ አንዳንዴ የምናየውን የሚቃጠል ወይ የሚወድም ንብረትን ግን ወደ ሕዝብ ሀብትነት ለውጦ ለነጻነት ትግሉ እንዲጠቅም ማድረግ ይቻላል፡፡ ማናቸውንም ከሀገርና ከሕዝብ የዘረፉትንና የሚዘርፉትን ንብረት ከማውደም በሕዝብ ቁጥጥር ሥር አውሎ ለትግሉ ስኬት እንዲያገለግል ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡ (በዚህ አንቀጽ ውስጥ የነበረና በሌሎች ድረገፆች ላይ ቀደም ሲል በስህተት የጠቀስኩት አንድ ነጥብ ነበር፡፡ (more…)