በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት 20 እስረኞች መገደላቸው ተሰማ | ቃጠሎውን የሚያሳይ አጭር ቪዲዮ ይዘናል

(ዘ-ሐበሻ) በዛሬው ዕለት በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት የተነሳውን የ እሳት ቃጠሎ ተከትሎ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ 20 እስረኞች መገደላቸው ተሰማ:: በቅሊንጦ እስር ቤት አንጋፋ ፖለቲከኞች እና የሃይማኖት መሪዎች የታሰሩ ሲሆን የሟቾች ማንነት እስካሁን እንዳልተለየ ከአካባቢው የመጡ መረጃዎች አስታውቀዋል::

14232050_188938048184896_4808177809913895242_o

በሃገር ቤት የሚታተመው አዲስ ፎርቹን ጋዜጣም 20 ሰዎች ስለመገደላቸው የዘገበ ሲሆን 3 የ እሳት አደጋ ሰራተኞች ቆስለው ሃኪም ቤት ገብተዋል ብሏል::

በቂሊንጦ የተነሳው የ እሳት ቃጠሎ ሆን ተብሎ በ ስር ዓቱ የተከፈተ ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ:: እነዚህ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ከዚህ ቀደም በተለያዩ ከተሞች የሕወሓት መንግስት ቦምቦችን በማፈንዳትና በ አልሸባብ በማሳበብ የውጪ ሃገራትን ድጋፍ ለማገኘት እንዳሴረ መዘገቡን አስታውሰው ባለፈው ሳምንት በሃረርጌ 2 መስጊዶች ላይ ቦምብ በመወርወርና ሰላማዊ ሰዎችን በመግደልና አሁን ደግሞ በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት እሳት በማፈንዳት ከሽብርተኝነት ጋር በማያያዝ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ያቀደው ሊሆን ይችላል ይላሉ::

በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት እንደነበቀለ ገርባ; እስክንድር ነጋና የመሳሰሉት ታዋቂ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች የሚገኙ ሲሆን ስለደህንነታቸው ለማወቅ የተደረገው ጥረት አልተሳካም::

ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ ከአዲስ አበባ የበቀለ ገርባ ባለቤትን አንገጋሮ እንደነበር በፌስቡክ ገጹ ዘግቧል:: የበቀለ ባለቤት ወሮ ሃና እንዳሉት ” በቀለም ሆነ ሌሎች በቂሊንጦ የሚገኙ እስረኞች በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ማወቅ አልቻልንም:: ከበቀለ ጋር ባሳለፍነው ሐሙስ ቂሊንጦ ተገናኝተን በሰላም ተነጋገረን ነበር። ትናንት ለጥየቃ መግባት አልቻልኩም። ዛሬ ልጃችን ቦንቱ ሄዳ ነበር። ረፋድ ላይ በቂሊንጦ በተነሳው ቃጠሎና ተኩስ ምክንያት ደውላለኝ ተነጋግረናል። ቀኑን ሙሉ በአከባቢው ብትገኝም አባቷን መጠይቅ ሳትችል ወደቤት ተመልሳለች። በቀለም ሆነ ሌሎች በቂሊንጦ እስር ቤት ያሉ ወገኖቻችን በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ማወቅ አልቻልንም። ነገ እኔና ልጄ ቂሊንጦ እንሄዳለን።

Posted on September 3, 2016, in Andinet, Andinet party, esat.com, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF, oromo. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: