አምባ ጊዮርጊስና ደብረታቦር በሁለት ቀናት ከ50 በላይ አማሮች ተገደሉ | በጎንደር የተደረገው ስብሰባ ያለውጤት ተበተነ | በደብረ ታቦር ዳግመኛ የቤት ውስጥ አድማ ተጠራ

የጠ/ሚውን አዋጅ ተከትሎ በመተማ፣ አምባ ጊዎርጊስና ደብረ ታቦር ከ50 በላይ ዐማሮች በሁለት ብቻ ቀናት ተገድለዋል

• በሽንፋ ከተማ የቀን ሠራተኞች በጥይት ተደብድበዋል
• በደብረ ታቦር ዳግመኛ የቤት ውስጥ አድማ ተጠራ
• በላሊባላ በግፍ ለተጨፈጨፉ ዐማሮች ጸለት ተደረገላቸው
• በጎንደር የተደረገው ስብሰባ ያለውጤት ተበትኗል

ከሙሉቀን ተስፋው

ጎንደር፤ የጠቅላይ ሚንስትሩን ‹‹በእኔ በኩል የጸጥታ አካላት ያለምንም ርህራሄ ማንኛውምን ኃይል እንደሚጠቀሙ አዝዣለሁ›› ማለታቸውን ተከትሎ ነሃሴ 25 እና 26 ቀን 2008 ዓ.ም. በመተማና በወገራ አካባቢዎች ከ45 በላይ ዐማሮች በትግሬ መከላከያ ኃይል ያለምንም ርህርራሄ ተጨፍጭፈዋል፡፡ ዛሬ ከመተማ ምስክረነታቸውን የሰጡን የዓይን እማኝ 19 ሰዎች በወታደር መገደላቸውን ተናግረዋል፡፡ በመተማ ዮሀንስ ከተማ 19 የሚሆኑት ዐማሮች አስከሬናቸው የታወቀ ሲሆን በጫካ ያልተገኙ ሁሉ ሊኖሩ እንደሚችሉ አስተያየት ሰጪው ተናግረዋል፡፡ ከ10 በላይ የሚሆኑ ዐማሮችም ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ተብለሏል፡፡
north Gonder

ይህ በዚህ እንዳለ ከሸኽዲ ከተማ ወደ ቋራ መንገድ ላይ ባለችው የሽንፋ ከተማ ደግሞ የቀን ሠራተኞች ቆመው በነበረበት ቁጥራቸው ያልታወቁ ዐማሮች በጥይት መደብደባቸውን ለማወቅ ችለናል፡፡ ሽንፋ ላይ ምንም በሌለበት የትግራይ መከላከያ ሠራዊት በቁሞበት በጥይት የደበደባቸው ሲሆን በከፍተኛ ቁስለት ላይ ያሉ የታሰሩ ሰዎችም አሉ ተብሏል፡፡
ወደ ወገራ ወረዳ ስንመለስ ደግሞ ከአንባ ጊዎርጊስ ወጣ ብሎ ጫካ ውስጥ ተደብቀን ነው ያለው አስተያየት ሰጪ እንደሚለው ባለፉት ሁለት ቀናት ከአራት ዓመት ሕጻን ጀምሮ ከ26 በላይ የአምባ ጊወርጊስ ዐማሮች በጥይት ተጨፍጭፈው ተገድለዋል፡፡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ወጣቶች ደግሞ በጥይት ቆስለውም በወገራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ውስጥ ታስረው ሕክምና ተነፍገው ይገኛል ብለውናል፡፡ 40 የሚሆኑ ወጣቶች ደግሞ ጎንደር ተወስደው ቶርቸር እየተደረጉ እንደሆነም እኚሁ እማኛችን ተናግረዋል፡፡ በአምባ ጊወርጊስ ብዙዎቹ በጥይት የተገደሉ ዐማሮች ሕጻናትና አቅመ ደካሞች መሆናቸውንም አስተያየቱን የሰጡን ሰው ተናግረዋል፡፡ በወገራ ወረዳ ወንድ የተባለ ሁሉ ከተማ እንደማይገኝ አክለው ተናግረዋል፡፡

ደብረ ታቦር፤ የደ/ ታቦር ማረሚያ ቤት ትናት ነሃሴ 26 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር በግምት ከ10፡00 ጀምሮ ምንነቱ ባልታወቀ ምክንያት በእሳት ተቃጠለ፡፡ በእሳት ሲቃጠል የትግሬ አጋዚ ሠራዊት የደረሱበት ጊዜ ነበር፡፡ ከውስጥ በእሳት ከውጭ ደግሞ በአጋዚ ጥይት አጣብቂኝ ውስጥ የገቡት የሕግ ታራሚዎች በእሳት ላለመበላት በሚያደርጉት ርብርብ አጋዚ ጥይት ተለቅመዋል፡፡ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ሁለት እስረኞች ብቻ በአጋዚ እንደተመቱ ይፋ ቢያደርግም እስከ ዛሬ ማታ ድረስ በሕይወት የተረፉትን በሕግ ጥላ ሥር ያሉ ታራሚዎች ለቤተሰቦቻቸው እንዳይገናኙ ከልክሎ ውሏል፡፡ ማረሚያ ቤቱ ባለበት ወይብላ በሚባለው ሠፈር ነው የምኖረው ያለን አስተያየት ሰጪ ከውጭ በወታደር እየተመቱ ይወድቁ የነበሩ ሰዎችን ማየቱን ተናግሯል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ በደብረ ታቦር፤ ወረታ፣ አዲስ ዘመንና ጋይንት እንዲሁም በአካባቢው ባሉት ከተሞች ከነሃሴ 29 ቀን እስከ ጳጉሜ 3 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ የሚቆይ የቤት ውስጥ አድማ ድጋሚ መጠራቱን ለማወቅ ችለናል፡፡ የቤት ውስጥ አድማውን በተመለከተ የሚበተነው ደብዳቤ እስከ ጳጉሜ 3 ቀን ቢልም እስከ መስከረም 10 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ ሊቆይ እንደሚችል በከተማው እየተወራ ነው፡፡ የፋርጣና የደብረ ታቦር ሕዝብ የምግብ እህል በማስፈጨት ላይ መሆኑንና አስፈላጊ የተባሉትን ሁሉ እየሸመቱ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡

ከደብረ ታቦር ሳንወጣ ለወያኔ በመሰለል አገልግሎት ይሰጣሉ የተባሉ የሕወሓት እና ቅጠረኛ አባላትን ስም ዝርዝር ከሕዝብ ጎን የተሰለፉ ፖሊሶችና የጸጥታ አካላት ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ ዛሬ በርካታ ነጋዴዎች፣ መምህራንና ወጣቶች መታሰራቸውን ጠቁመው ሥርዓቱ በተስፋ መቁረጥ እየተንገታገተ እንዳለ ማስረጃ ነው ሲሉ አስተባባሪዎች ተናግረዋል፡፡
ላሊበላ፤ በላሊበላ ከተማ በሁሉም አድባራት ዐማራ በመሆናቸው ብቻ ስለተገደሉ ሰዎች ጸሎትና ምኅላ ተደርጓል ተብሏል፡፡

ደሴ፤ በደቡብ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች ከፍተኛ የትግሬ ወታደር እና ሰላይ ተሰማርቶ ሕዝቡን እያስፈራራ በመሆኑ ዜጎች መሳቀቃቸውን ገልጸዋል፡፡ በኮምቦልቻ ከተማ በቀጣይ ሳምንት የቤት ውስጥ አድማ ለማድረግ ወረቀት እየተበተነ ነው፡፡ በሁሉም የደቡብ ወሎ አካባቢዎች ደግሞ የወልቃይት ጥያቄ የዐማራ ሕዝብ ጥያቄ አይደለም፤ የጠቅላይ ሚንስተሩ ትእዛዝ ትክክለኛ ነው በሚሉ ጉዳዮች ላይ ነዋሪች ቢሰበስቡም አንዳንድ ወረዳወች ላይ ስብሰባውን ረግጠው መሔዳቸው ተሰምቷል፡

Posted on September 3, 2016, in Andinet, Andinet party, esat.com, ETHIOPIA AMHARIC, Ginbot 7, OLF, oromo. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: