Category Archives: AFRICAN NEWS

ወልቃይት፣ ያሬድ ጥበቡና ጄኔራል ጻድቃን (በፍቃዱ ደረጀ)

በፍቃዱ ደረጀ

  • ጻድቃን እንደ እኛ ሊያስብ ይችላል፣
  • ህጋዊ ማእቀፎችን እንጠቀም፣
  • አዲስ አበባ አድጋለች መጎብኘት ባልችልም፣
  • የመለስ ጥሩ ስራ ህወሀትን ከሌሎች ድርጅቶች እኩል አድርጎት መሄዱ ነው

ያሬድ ጥበቡ ኢህዴን የተባለውን ብአዴን ከመሰረቱ ግለሰቦች አንዱ ነበር ሲታገል ሲታገል ቆየና ከእለታት አንድ ቀን የአመት እረፍት ተሰጠው ይህንን የእረፍት ጊዜውን በዋና እንደሚያሰልፍ ቀድሞ የተረዳው ወዲ ዜናዊ ተከዜ ላይ ለምን አንዋኝም ሲል ግብዣ አቀረበለት ሳያቅማማ ተቀበለው የመለስ ዜናዊ ጦር እየወጋው ቢሆንም ያሬድ አንዳች ነገር ሳይሰማው ወደ ተከዜ ወንዝ ተጓዘ እንደደረሱም ጨዋታ ፈረሰ ዳቦ ተቆረሰ ከዛሬ ጀምሮ የኢህዴን አመራር አይደለህም ሁለት ምርጫዎች አቀረበለት… ብርሀኑ ነጋ የሄደበትን መንገድ መርጦም በፓርት ሱዳን አድርጎ ዲሲ መኖር ከጀመረ 30 አመት ሊሞላው የጳጉሜን መጥባት እየተጠባበቀ ነው። (more…)

በስደት ላይ ያለው ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አንድነት ማህበር የአቋም መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን።

በስደት ላይ ያለው ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ በቅርቡ በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳይ ዙሪያ የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት መነሻ በማድረግ ያወጣውን መግለጫ በመደገፍ በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አንድነት ማህበር የተሰባሰብን ተወካዮች ባካሄድነው አስቸኳይ ጉባኤ በሀገራችን ኢትዮጵያ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በሰፊው ተመልክተን የጋራ የአቋም መግለጫ አውጥተናል። (more…)

(ሰበር ዜና) – በጎንደር ለምን ነጭ በነጭ ለበሳችሁ በሚል የትግራይ ነጻ አውጪ አልሞ ተኳሽ በወሰደው እርምጃ 4 ሰዎች በጥይት ተገደሉ

August 20, 2016

በዛሬው እለት በጎንደር የአምባገነኑን መለስ ዜናዊን ሙት ዓመት አናከብርም ብለው ነጭ ልብስ በመልበሳቸው በአልሞ ተኳሾች ከተገደሉት 4 ሰወች አንደኛው::

በዛሬው እለት በጎንደር የአምባገነኑን መለስ ዜናዊን ሙት ዓመት አናከብርም ብለው ነጭ ልብስ በመልበሳቸው በአልሞ ተኳሾች ከተገደሉት 4 ሰወች አንደኛው::

(ዘ-ሐበሻ) በዛሬው እለት ጎንደር ከተማ የአቶ መለስ ዜናዊን ሙት ዓመት አናከብርም በሚል ለተቃውሞ ነጭ በነጭ ከለበሱት መካከል በአጋዚ ሰራዊት 4 ሰዎች በጥይት ተደብድበው ተገደሉ:: የአጋዚ ጥይት ሰለባ ከሆኑት መካከል አንዱ ወጣት ፎቶ በማሳት የሚተደደር ወጣት ግዛቸው የሚባል እንደሆነና ለምን ነጭ ልብስ ለበስክ በማለት ቀበሌ 03 አስተዳደር አካባቢ ከጓደኞቹ ነጥለው በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ደብድበው ከገደሉት በኋላ አስከሬኑን ወደ ጎንደር ሆስፒታል ወስደው ጥለውት ተገኝቷል ሲሉ ዘ-ሐበሻ ያነጋገረቻቸው የአይን እማኞች ገልጸዋል:: (more…)

ጀግናው የጎንደር፤ የጎጃም፤ የሸዋና የወሎ አማራ ህዝብ ሆይ (ዶ/ር ደጀኔ አለማየሁ ላቀው)

ዘርህን፤ ሃገርህንና ማንነትህን ከጥፋት ለመጠበቅ ላለፉት ሳምንታት ያሳየሃቸዉን የጀግንነት የብልህነትና የሃገር ወዳድነት እርምጃ በጽሞና መላው አለም አይቷል። ኢትዮጵያም የተደፋ አንገቷን ቀና አድርጋ አይታለች፤ ተደስታለች፤ በርግጥም ልጆቸ አሉ ብላለች። በቅርቡም እነሳለሁ፤ እንደገናም አብባለሁ ብላለች። (more…)

ኢሀዴግ እና ስብሰባ

august 18 08 2016

መንግስት ተቃውሞው በአዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ በስጋት ተወጥሯል
ዋዜማ ራዲዮ- መንግሥት በአዲስ አበባ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችና የሥራ ማቆም አድማ ሊስፋፋ ይችላል የሚል ስጋቱ አይሎበታል። ይህን ተከትሎ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሠራተኞች ስብሰባ እየተጠሩ ነው። የመንግሥት ተቀጣሪ ያልሆነውን የከተማ ነዋሪ ደግሞ በኢሕአዴግ እና በመንግሥት መዋቅሮች በተከታታይ ለመሰብሰብ መታቀዱ ተሰምቷል። (more…)

ጊዜዉ ደረሰ (ፊዳ ቱምሳ)

 August 17, 2016

ፊዳ ቱምሳ

ዕንባ እየተናነቀኝ የዛሬዉ የኦሮሞ ትዉልድ እየከፈለ ያለዉን መስዋዕትነት ከእሱ ጋር ሆኜ ያለመካፈሌ እያንገበገበኝ ተከዝኩ፡፡ የነፃነት ቀን መቃረቡን ሣይ በአንድ በኩል እጅግ ተፅናናሁ፡፡ የነገዉን ነፃነት ሳያዩት ለመጪዉ ትዉልድ የተሰዉትን ጀግኖች በዓይኔ እየዳሰስኩ ኮራሁባቸዉ፡፡ የእነርሱ ደም የፈሰሰዉ በከንቱ እንዳልሆነ ስረዳ በእጅጉ ተፅናናሁ፡፡ በልጅነት ዕድሜአቸዉ ለዚህ ታላቅ መስዋዕትነት ራሳቸዉን መስጠታቸዉ ለትዉልድ መዘከር የሚገባዉ ታሪክ እንደሆነ ያለጥርጥር ከህሊናዬ ጋር ተስማማሁ፡፡ እንደገናም ወደኋላ ሄጄ ያለፍንበትን መንገድ እንድመለከት አዕምሮዬ ሞገተኝና ተጓዝኩ — የህሊና ጉዞ፡፡

Ethiopia, TPLF officials

“Whoever sows injustice will reap calamity.”

ጊዜዉ 1991 ዓ.ም. ነበር፡፡ የነበርኩት ጀርመን አገር በርሊን ከተማ ዉስጥ ነበር፤ በጊዜዉ የኦሮሞ ከተማ!! የወያኔ ሠራዊት ጎጃምን ተሻግሮ ወደ ኦሮሚያ ሲገሰግስ ተቃወምን፣ አወገዝን፤ ቀጥሎም ነቀምት መግባታቸዉን ሲለፍፉ የተቃዉሞ ሰልፍ አዘጋጀን፡፡ የተቃዉሞ ሰልፉ መነሻ ነቀምት ከመግባታቸዉ ጋር የሰጡት መግለጫ ነበር፡፡ መግለጫዉን እንደማስታዉሰዉ “ወተት ጠጣን ጮማ በላን” የሚል እና በዚህ መንገድ ተስተናገድን የሚል መግለጫ ነበር፡፡ ይሄ መግለጫ ወደፊት ለታቀደዉ ብዝበዛና ምዝበራ ሀ ሁ መሆኑን ስለተገነዘብን ነበር ተቃዉሞ ያዘጋጀነዉ፡፡ እናም በተቃዉሞዉ ሰልፍ ላይ የሚሰራጭ ወረቀት እንዲዘጋጅ ተወስኖ አንድ ጓደኛችን ወረቀቱን አዘጋጅቶ አመጣ፡፡ በጽሑፉ ዉስጥ የተቀመጠዉ ምሳሌያዊ መልዕክት ዛሬ ይህን እንድጽፍ አስገደደኝ፡፡

ምሳሌያዊዉ መልዕክት እንዲህ ይላል:- “አንድ በበረሃ የተጎሳቆለ እባብ በጠርሙስ ዉስጥ ያለ ወተት አይቶ ወተቱን ለመስረቅ ዙሪያዉን ተጓዘ፤ አልቻለም፡፡ እናም ጠርሙሱ ዉስጥ ገብቶ ለመጠጣት በዚያ በከሣ አካሉ በጠርሙሱ አፍ ወደ ጠርሙሱ ገባ፤ ወተቱን እየጠጣም ወፈረ፤ ከጠርሙሱ ለመዉጣት የገባበት የጠርሙስ አፍ ከዉፍረቱ የተነሣ አያስወጣዉም፡፡ እናም ሁለት አማራጭ ብቻ ቀረዉ፤ ወይ ወተቱን ተፍቶ መዉጣት ወይ ጠርሙሱ ዉስጥ መሞት፡፡” እናም ያ ጽሑፍ ወያኔ ወደ ኦሮሚያ ገባ፤ ምርጫዉ የዚያ እባብ ምርጫ ብቻ ይሆናል ይላል፡፡ ለወያኔ የያኔዉ መልዕክት ሳትጠራ ወደ ኦሮሚያ አትግባ፤ ኦሮሚያ የራሱ አባት አለዉ፤ ባለቤት አለዉ የሚል ነበር፡፡ ከገባህ ደግሞ ዕጣ ፈንታህ የእባቡ ዕጣ ፈንታ ነዉ፤ ወይ እዚያዉ ትቀበራለህ፣ ወይ በመጣህበት ሁኔታ ወደመጣህበት ትመለሳለህ የሚል ነበር፡፡

ከሃያ-አምስት ዓመት በኋላ ዛሬ የኦሮሞ ሕዝብ ተነስቷል፤ የኦማራ ሕዝብ ተነስቷል፡፡ ወያኔ በእነዚህ ሕዝቦች ተከቦአል፤ እባቡ በጠርሙሱ እንደተከበበዉ፡፡ ወተቱን ጠጥቶ እንደወፈረዉ እባብ ወያኔ ወፍሯል፤ ሀብት ዘርፎአል፣ ተንጠባሯል፡፡ እናም እንደእባቡ ሁሉ ጠርሙሱን ለመስበር ይንፈራገጣል፡፡ ጠርሙሱ ግን አይሰበርም፤ የተጠናከረ የተባበረ ሕዝባዊ ኃይል ነዉና፡፡ ጠርሙሱን የከበቡት የኦሮሞ የአማራና የሌሎች ህዝቦች የነፃነት ሃይሎች ኢሳት አቀጣጥለዋል …. ጠርሙሱም እየጋለ ነው ፤ የወያኔ ምርጫ እንግዲህ እንደ እባቡ ሁሉ የበላዉን ተፍቶ፣ የዘረፈዉን ትቶ መዉጣት፤ አለያም እንደበላ እንደወፈረ መቃጠልና መሞት ነዉ፡፡ መዉጫ ቀዳዳ የለም፡፡ በህፃናት ደም ተጨማልቆ፣ በእናቶች ደም ተጨማልቆ፣ በከበሩ አዛዉንቶች ደም ተጨማልቆ የደም ካሣ ሣይከፍሉ ወዴት ይኬዳል? ይዋል ይደር እንጂ የእባቡ ምሳሌ ጊዜዉ ደረሰ፤ ጠርሙሱም ከተሰባሪ ጠርሙስነት ወደ ብረት ጠርሙስነት ተሸጋገረ፤ እባቡም ተከበበ፡፡ እንደገናም ጊዜዉ ደረሰ፡፡

August 6, 2016 (አመሻሽ)

የት ናችሁ የትግራይ ልሂቃን? (ከአንተነህ መርዕድ)

በስማችሁ የተደራጀው ዘረኛና ዘራፊ ቡድን የንፁህ ኢትዮጵያን ልጆች ደም እንደጎርፍ ሲያፈስስ ምነው ድምፃችሁ ጠፋ?

የኦጋዴኖች መጨፍጨፍና ሬሳቸው በሜዳ ላይ መጎተት፣ የጋምቤላዎች በጅምላ መታረድ፣ የኦሮሞዎችና የአማራዎች በጠራራ ፀሃይ በአነጣጥሮ ተኳሽ ትግርኛ ተናጋሪ አጋዚ በየሜዳው መደፋት እንዴት ህሊናችሁን አልኮሰኮሳችሁም? (more…)

[must read] Eritrea torturing OLF and in the process of forming a new OPDO

Journey in the dark Oromo’s untold story in Eritrea…. Read the rest of this entry

Yemen migrant boat carrying Ethiopians sinks killing 70

 

Migrants waiting to board a boat to Yemen in Djibouti
Tens of thousands make the dangerous journey every year

Related Stories

A boat carrying African migrants has sunk off Yemen’s western coast, killing 70 people, Yemeni officials say… Read the rest of this entry

Ethnic Cleansing of Amhras in Wollega, Western Ethiopia

By Dimetros Birku    Clear early omens of ethnic cleansing are unfolding in Western Ethiopia. Gimbi, a small town west of Wellega, in what is now Oromia regional state, was a scene of attack on residents of the town who happened to be Amharic speakers.. Read the rest of this entry

%d bloggers like this: