Category Archives: oromo

ከሰሜን ጎንደር የአማራ ሕዝብ ትግል አስተባባሪዎች ለምሊሻ ታጣቂዎችና ለመላው የአማራ ሕዝብና ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያዊ ወገናችን ሁሉ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ

north Gonderሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ሰሞኑን በተደጋጋሚ እንደዛተው የአማራን ክልል የጦርነት ቀጠና አደርጋለሁ ብሎ ተግባራዊ አድርጓል። ንጹሃን የአማራ ተወላጆችን ህጻናትን ጨምሮ ያለርህራሄ ባሰማራው አጋዚ ታጣቂዎች እያስገደለ ይገኛል።የሕዝባዊ ወያኔ መሪዎች የአጋዚ ጦር ብቻ ሳይሆን በሀሰት የገበሬ ታጣቂዎችን ጭምር <<አባይ እንዳይገደብ የሚፈልጉ የሻዕቢያና የኤርትራ ተላላኪዎች ናቸው>> በሚል ወገን ወገኑ ላይ እንዲተኩስ አበል እየከፈሉ መሳሪያ እያስታጠቁ ጭምር አሰማርተዋል። ይሄ ብዙ ርቀት አይወስዳቸውም።ሐቁን የአማራ ምሊሻ ይረዳል።ያውቃል።ሕወሓት በአማራ ሕዝብ ላይ ወልቃይት የአማራ ነው በማለቱ ለሰላማዊ ተቃውሞ የሰጠው የጥይት ምላሽ ሰጥቷል። (more…)

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት 20 እስረኞች መገደላቸው ተሰማ | ቃጠሎውን የሚያሳይ አጭር ቪዲዮ ይዘናል

(ዘ-ሐበሻ) በዛሬው ዕለት በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት የተነሳውን የ እሳት ቃጠሎ ተከትሎ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ 20 እስረኞች መገደላቸው ተሰማ:: በቅሊንጦ እስር ቤት አንጋፋ ፖለቲከኞች እና የሃይማኖት መሪዎች የታሰሩ ሲሆን የሟቾች ማንነት እስካሁን እንዳልተለየ ከአካባቢው የመጡ መረጃዎች አስታውቀዋል::

14232050_188938048184896_4808177809913895242_o

በሃገር ቤት የሚታተመው አዲስ ፎርቹን ጋዜጣም 20 ሰዎች ስለመገደላቸው የዘገበ ሲሆን 3 የ እሳት አደጋ ሰራተኞች ቆስለው ሃኪም ቤት ገብተዋል ብሏል:: (more…)

የኦሮሞው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ለምን ገብ አለ? | ጥበቡ ታዬ

አንድ የሕዝብ እንቅስቃሴ ለመነሳት ምክንያት አለው፣ለመቆምም እንዲሁ።ብሶትና ምሬት የሕዝብን እምቢባይነት ይቀሰቅሳል።እንቅስቃሴው ከተሳካ በድል ይጠናቀቃል፤ አለዚያም በመንግሥት ሃይል የጥቃት እርምጃ ለጊዜው ሊገታ ይችላል። በዚህ መልክ የሚረጋገጥ የበላይነት ቂምን ስለሚወልድ ቅራኔውና ትግሉ እስከነአካቴው አይጠፋም።ጊዜ ጠብቆ ያገረሻል።ሌላው ምክንያት ደግሞ በመንግሥትና በተነሳው ሕዝብ መካከል ውይይት ተካሂዶ ሕዝቡ የሚፈልገውን እንደሚያገኝ የተስፋ ቃል ተሰጥቶትና ያንን ተቀብሎ ከተነሳበት እንዲያፈገፍግ የሚያደርግ ስራም ከተሰራ የሕዝብን ትግል ሊገታው ይችላል። (more…)

 

ዐርብ ነሐሴ 27 ቀን 2008 ዓ.ም

file photo

አዲስ አበባ ውስጥ በቤት ውስጥ በመቀመጥ መንግስትንየመቃወም ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን የሃይማኖት አባቶች ለመንግስት ገለጹ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት አሥራ አምስት ቀናት መንግስት ከወትሮ በተለየ ሁኔታ በማዘጋጃ፣ በክፍለ ከተሞችና በወረዳወች የእያንዳንዱን ሃይማኖት ቤተ አምልኮ መሪዎችን በመሰብሰብ ውይይት ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡

(more…)

የሕግ ባለሙያዎች ታሪክና ግዜ የጣሉባችሁን ኃላፊነት እንደምትወጡ ይጠበቃል! [በላይነህ አባተ]

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

justiceታሪክና ግዜ በትውልድ ኃላፊነትን ይጥላል፡፡ ይህ ትውልድ በሮማውያን ዘመን ኃላፊነቱን በሚገባ እንደተወጣው ትውልድ ታሪክና ግዜ ኃላፊነት ጥለውበታል፡፡የሮማውያንን ተደጋጋሚ ጪፍጨፋ አያት ቅደመ-አያቶቻችን በሚያስደንቅ ጀብዱ መክተውታል፡፡ ከሮማውያን ቅኝ ገዥዎች ጪፍጨፋ በከፋ ሁኔታ በእጅ አዙር ቅኝ ገዥ አገልጋዮች ህጻናት ጭንቅላታቸውን በላውንቸር እንደሚበረቀሱ፣ እግራቸውን በባሩድ እንደሚቆረጡና ሆዳቸውን እንደሚዘረገፉ አምባ ጊዮርጊስ በዚች ቅጽበት አስገንዝቦናል፡፡ እነዚህን የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ አገልጋይ ጨፍጫፊ ባንዳዎችም ሕዝብ ግብግብ ገጥሟቸው ይገኛል፡፡ ይህ የጪፍጨፋ ግዜ ከገዳዮች የወገነውን እርጉሞችና ድምጣችንን አጥፍተን እንጀራችንን የምናሳድደውን አድርባዮች በትዝብት ቴሌስኮፕ ይመለከተናል፡፡ (more…)

አምባ ጊዮርጊስና ደብረታቦር በሁለት ቀናት ከ50 በላይ አማሮች ተገደሉ | በጎንደር የተደረገው ስብሰባ ያለውጤት ተበተነ | በደብረ ታቦር ዳግመኛ የቤት ውስጥ አድማ ተጠራ

የጠ/ሚውን አዋጅ ተከትሎ በመተማ፣ አምባ ጊዎርጊስና ደብረ ታቦር ከ50 በላይ ዐማሮች በሁለት ብቻ ቀናት ተገድለዋል

• በሽንፋ ከተማ የቀን ሠራተኞች በጥይት ተደብድበዋል
• በደብረ ታቦር ዳግመኛ የቤት ውስጥ አድማ ተጠራ
• በላሊባላ በግፍ ለተጨፈጨፉ ዐማሮች ጸለት ተደረገላቸው
• በጎንደር የተደረገው ስብሰባ ያለውጤት ተበትኗል
(more…)

የኢትዮጵያ ነብሮች ሲበሳጩ ያጉረመርማሉ! (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ አሜሪካውያን የጀግንነት በላይነት የላቸውም፣  ማለትም  የኦሎምፒክ ጀግንነት ጠቅላይነት፡፡ እ.ኤ.አ ነሐሴ 21/2016 የ26 ዓመቱ የኢትዮጵያ የረዥም ርቀት ማራቶን ሯጩ ፈይሳ ሌሊሳ በአንድ ወቅት በኦሎምፒክ ጨዋታዎች ታሪክ “የኦሎምፒክ ጨዋታዎች የፖለቲካ እንቅስቃሴ መግለጫ መድረኮች ሊሆኑ አይችሉም” በማለት ይገለጽ የነበረውን ሕግ ወደ ጎን አሽቀንጥሮ በመጣል በሪዮ ኦሎምፒክ ውድድር አስደናቂ የሆነ ታሪካዊ ድርጊትን ደግሟል፡፡ እ.ኤ.አ ጥቅምት 16/1968 በሜክሲኮ ኦሎምፒክ ተደርጎ በነበረው የ200 ሜትር የአጭር ርቀት የሩጫ ውድድር ቶሚ ስሚዝ እና ጆን ካርሎስ የወርቅ እና የብር ሜዳሊያ አሸናፊዎች ሆነው ነበር፡፡ በሜዳሊያ አሰጣጥ ስነስርዓት መድረኩ ላይ አድርገውት የነበረው ታሪካዊ ድርጊት በአሁኑ ጊዜ ትልቅ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ይገኛል፡፡ የእጆቻቸውን ቡጢዎች ከፍ አድርገው ከራሳቸውበ በላይ ወደ ላይ በማንሳት የጥቁር ሕዝቦችን አይበገሬነት ምልክትነት በይፋ አሳይተዋል፡፡ ፈይሳ ከውድድሩ ማጠናቀቂያ መስመር ላይ ሲደርስ ሁለቱንም እጆቹን አጣምሮ ከእራሱ በላይ ከፍ አድርጎ በማንሳት የኢትዮጵያን ወጣቶች የአይበገሬነት የኃይል ምልክት እንቅስቃሴ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በይፋ አሳይቷል፡፡ (more…)

የሕዝብን አመጽ የሚያሸንፍ ኃይል የለም! (ይፍሩ ኃይሉ)

በይፍሩ ኃይሉ

በቅርቡ ”ጎንደር፤ እሳቱን በሣት ያጠፋ ጀግና ነው “ በሚል አረዕስት ባቀረብኩት ሐተታ ውስጥ የወልቃይት ጠገዴን የማነት ጥያቄ ተመርኩዤ ነበር። በዚያ ላይ የጎንደር ቁጣና ያስከተለው፤ ከአትናፍ እስከ አጥናፍ የተቀጣጥጠለ የሕዝብ በውልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ላይ ብቻ የተወሰነ ሣይሆን፤የመላው የኢትዮጵያን ሕዝብ የልብ ትረታንና ብሶት የነካ በዉድም ሆነ በግድ ወያኔ ከሥልጣን መውረድ አለበት የሚል ነው ። ከእንግዲህ የወያኔን የግፍ ቀንበር የምንሸከምበት ጫንካችን ትልጧልና ከትከሻችን በፍጥነት ይዉርድልን” እያለ ነው የሚጮኸው። ይህ ገና የመጀመሪያው “በቅቶኛልና የአዳምጠኝ” ጩኸት እንጂ ወያኔ የኢትዮጵያ ሕዝብ የደገሰለትን ያወቀው አይመስለኝም። እንደለመደው ያችኑ ያችን የከፋፍለህ ግዛ ዘዴውን እንዳይጠቀም ጎንደር ከኦሮሞው ከመራቁም በላቅይ ‘ የኦሮሞ ሕዝብ ስቃይ የኔም ስቃይ ነው፤ የኦሮሞ ደም ሲፈስ የኔ ደም እንደፈሰሰ እቆጥረዋለሁ “ እያለ ሰንደቁን አንግቦ ሲጮሕበት ወያኔ ወዴት ይሩጥ? ግን ያንኑ የፈረደበትን የትግራይን ሕዝብ ከማወናበድ አልጠቆጠበም። ጥቂት የአማራ ሆዳሞችና ለላንቲካ የተቀመጠው ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ፤”ወልቃይት የትግራይ አካል ለመሆኗ ታሪክ ይመስክራል..” እያሉ ማንዛረጥ ጀመሩ።የጎንደር ሕዝብና የኢትዮጵያ የታሪክ ምሁራን ከት ብለው ሳቁ አሁንም እየተንከተከቱ ነው። የወያኔ የቅርብ ወገኖቹና የቀድሞ ታጋዮቹ፤”የደም ዋጋህ ነው” እየተባለ፤ከድሃ እየተነጠቀ ዛሬ ባለቪላ፤ ባለብዙ መኪና፤ባለ ብዙ ኃብት፤አብሮ ከወያኔ ጋራ ወልቃይት ጥገዴም ላይ ሆነ በሥላን ሙጥኝ ማለት ለኔ ይገባኛል ቢል አይፈረደበትም። ከሃያ አምስት ዓመት በፊት ለግሩ ጫማ ያልነበረው፤ዛሬ የግሩ ጫማ ከጣሊያንና ከስፔይን፤ ከአሜሪካና ከእንግሊዝ የመጣ ነው። የዛሬ ሃያ አምስት ዓመት የወያኔ ተጋድይ፤ቁርሱን በልቶ ለምሳውና ለራት፤”ከየት ይመጣ ይሆን?” እያለ ሲጨነቅ የኖረ፤ዛሬ እምብርቱ እስኪገለበጥ በዚግኒና በጢብሲ፤በዶሮወጥና በምንቸት አብሽ ይቀበተታል። ጮማ እንደጎመን የቆርጣል።የኢትዮጵያ ድሃ በጠኔ ሲሰቃይ፤ ወያኔ በቁንጣን ሲፈራገጥ ያድራል። እንኳን ቀምሶት ሰምቶት ያማያውቀውን ዊስኪና ብራንዲ፤ሻምፔኝና ዉድ የወይን ጠጅ ይጎንጫል።ጢንቢራው እስክዞር ድርስ ሰክሮ፤ በየቡና ቤቱ ሽንቱን በሱሪው ላይ ያንዠቀዠቀ፤ ከኪሱ ሽጉጡን አውጥቶ በሰው መያል ጥይት ይተኩሳል። ጸጥታ አስከባሪው ጸጥታውን ያደፈርሳል። የዚህ ዓይነት ባለጌ ከዚህ  ከተንጠለጠለበት ኮርቻ በፈቃዱ ይወርዳል ማለት ዘበት ነው። “ዋይ!ከዚህ ወርጄ እንደገና አጸበለስ ለቀማ የምሄደው?” ነው የሚለው። ይህ የሚወገደው በግድ ገባር ግንብሩን እያሉ በማጋደም ብቻ ነው። ሚያሳዝነው፤ከማራው፤ ከኦሮሞውና ከሌላውም ብሔረሶቦች ተውጣተው፤ከወያኔ ጋራ ለግል ጥቅም ሲሉ ብቻ፤ወገኖቻቸውን ሲገድሉና ሲያስገድሉ፤ከወያኔ ጋራ አብረው ሲዘርፉ የኖሩ ባንዳዎች ዛሬ መሬ ተከፍታ ብትዉጣቸው ይሻላል። ቀኑ የመሸው ለወያኔ ብቻ አይደለም ለሱም ጭምር ነው። ዛሬ እነሱና ወያኔ የታሰፈሩበት መርከብ ይዙዝቸው ሊሰምጥ ከዉቂያኖስ ላይ እየዋለለ ነው።Revolt in Ethiopia (more…)

በስደት ላይ ያለው ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አንድነት ማህበር የአቋም መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን።

በስደት ላይ ያለው ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ በቅርቡ በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳይ ዙሪያ የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት መነሻ በማድረግ ያወጣውን መግለጫ በመደገፍ በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አንድነት ማህበር የተሰባሰብን ተወካዮች ባካሄድነው አስቸኳይ ጉባኤ በሀገራችን ኢትዮጵያ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በሰፊው ተመልክተን የጋራ የአቋም መግለጫ አውጥተናል። (more…)

ጊዜዉ ደረሰ (ፊዳ ቱምሳ)

 August 17, 2016

ፊዳ ቱምሳ

ዕንባ እየተናነቀኝ የዛሬዉ የኦሮሞ ትዉልድ እየከፈለ ያለዉን መስዋዕትነት ከእሱ ጋር ሆኜ ያለመካፈሌ እያንገበገበኝ ተከዝኩ፡፡ የነፃነት ቀን መቃረቡን ሣይ በአንድ በኩል እጅግ ተፅናናሁ፡፡ የነገዉን ነፃነት ሳያዩት ለመጪዉ ትዉልድ የተሰዉትን ጀግኖች በዓይኔ እየዳሰስኩ ኮራሁባቸዉ፡፡ የእነርሱ ደም የፈሰሰዉ በከንቱ እንዳልሆነ ስረዳ በእጅጉ ተፅናናሁ፡፡ በልጅነት ዕድሜአቸዉ ለዚህ ታላቅ መስዋዕትነት ራሳቸዉን መስጠታቸዉ ለትዉልድ መዘከር የሚገባዉ ታሪክ እንደሆነ ያለጥርጥር ከህሊናዬ ጋር ተስማማሁ፡፡ እንደገናም ወደኋላ ሄጄ ያለፍንበትን መንገድ እንድመለከት አዕምሮዬ ሞገተኝና ተጓዝኩ — የህሊና ጉዞ፡፡

Ethiopia, TPLF officials

“Whoever sows injustice will reap calamity.”

ጊዜዉ 1991 ዓ.ም. ነበር፡፡ የነበርኩት ጀርመን አገር በርሊን ከተማ ዉስጥ ነበር፤ በጊዜዉ የኦሮሞ ከተማ!! የወያኔ ሠራዊት ጎጃምን ተሻግሮ ወደ ኦሮሚያ ሲገሰግስ ተቃወምን፣ አወገዝን፤ ቀጥሎም ነቀምት መግባታቸዉን ሲለፍፉ የተቃዉሞ ሰልፍ አዘጋጀን፡፡ የተቃዉሞ ሰልፉ መነሻ ነቀምት ከመግባታቸዉ ጋር የሰጡት መግለጫ ነበር፡፡ መግለጫዉን እንደማስታዉሰዉ “ወተት ጠጣን ጮማ በላን” የሚል እና በዚህ መንገድ ተስተናገድን የሚል መግለጫ ነበር፡፡ ይሄ መግለጫ ወደፊት ለታቀደዉ ብዝበዛና ምዝበራ ሀ ሁ መሆኑን ስለተገነዘብን ነበር ተቃዉሞ ያዘጋጀነዉ፡፡ እናም በተቃዉሞዉ ሰልፍ ላይ የሚሰራጭ ወረቀት እንዲዘጋጅ ተወስኖ አንድ ጓደኛችን ወረቀቱን አዘጋጅቶ አመጣ፡፡ በጽሑፉ ዉስጥ የተቀመጠዉ ምሳሌያዊ መልዕክት ዛሬ ይህን እንድጽፍ አስገደደኝ፡፡

ምሳሌያዊዉ መልዕክት እንዲህ ይላል:- “አንድ በበረሃ የተጎሳቆለ እባብ በጠርሙስ ዉስጥ ያለ ወተት አይቶ ወተቱን ለመስረቅ ዙሪያዉን ተጓዘ፤ አልቻለም፡፡ እናም ጠርሙሱ ዉስጥ ገብቶ ለመጠጣት በዚያ በከሣ አካሉ በጠርሙሱ አፍ ወደ ጠርሙሱ ገባ፤ ወተቱን እየጠጣም ወፈረ፤ ከጠርሙሱ ለመዉጣት የገባበት የጠርሙስ አፍ ከዉፍረቱ የተነሣ አያስወጣዉም፡፡ እናም ሁለት አማራጭ ብቻ ቀረዉ፤ ወይ ወተቱን ተፍቶ መዉጣት ወይ ጠርሙሱ ዉስጥ መሞት፡፡” እናም ያ ጽሑፍ ወያኔ ወደ ኦሮሚያ ገባ፤ ምርጫዉ የዚያ እባብ ምርጫ ብቻ ይሆናል ይላል፡፡ ለወያኔ የያኔዉ መልዕክት ሳትጠራ ወደ ኦሮሚያ አትግባ፤ ኦሮሚያ የራሱ አባት አለዉ፤ ባለቤት አለዉ የሚል ነበር፡፡ ከገባህ ደግሞ ዕጣ ፈንታህ የእባቡ ዕጣ ፈንታ ነዉ፤ ወይ እዚያዉ ትቀበራለህ፣ ወይ በመጣህበት ሁኔታ ወደመጣህበት ትመለሳለህ የሚል ነበር፡፡

ከሃያ-አምስት ዓመት በኋላ ዛሬ የኦሮሞ ሕዝብ ተነስቷል፤ የኦማራ ሕዝብ ተነስቷል፡፡ ወያኔ በእነዚህ ሕዝቦች ተከቦአል፤ እባቡ በጠርሙሱ እንደተከበበዉ፡፡ ወተቱን ጠጥቶ እንደወፈረዉ እባብ ወያኔ ወፍሯል፤ ሀብት ዘርፎአል፣ ተንጠባሯል፡፡ እናም እንደእባቡ ሁሉ ጠርሙሱን ለመስበር ይንፈራገጣል፡፡ ጠርሙሱ ግን አይሰበርም፤ የተጠናከረ የተባበረ ሕዝባዊ ኃይል ነዉና፡፡ ጠርሙሱን የከበቡት የኦሮሞ የአማራና የሌሎች ህዝቦች የነፃነት ሃይሎች ኢሳት አቀጣጥለዋል …. ጠርሙሱም እየጋለ ነው ፤ የወያኔ ምርጫ እንግዲህ እንደ እባቡ ሁሉ የበላዉን ተፍቶ፣ የዘረፈዉን ትቶ መዉጣት፤ አለያም እንደበላ እንደወፈረ መቃጠልና መሞት ነዉ፡፡ መዉጫ ቀዳዳ የለም፡፡ በህፃናት ደም ተጨማልቆ፣ በእናቶች ደም ተጨማልቆ፣ በከበሩ አዛዉንቶች ደም ተጨማልቆ የደም ካሣ ሣይከፍሉ ወዴት ይኬዳል? ይዋል ይደር እንጂ የእባቡ ምሳሌ ጊዜዉ ደረሰ፤ ጠርሙሱም ከተሰባሪ ጠርሙስነት ወደ ብረት ጠርሙስነት ተሸጋገረ፤ እባቡም ተከበበ፡፡ እንደገናም ጊዜዉ ደረሰ፡፡

August 6, 2016 (አመሻሽ)

%d bloggers like this: