Blog Archives

ታሪክን በመሰረዝና በመደለዝ ማስተካከል አይቻልም (ያማራ ድምፅ)

ጥሩም ይሁን መጥፎ ታሪክን በመሰረዝና በመደለዝ ማስተካከል አይቻልም።ሁላችንም እንደምናውቀው ላለፈው ሃያ ሁለት ዓመት የወያኔ ዘረኛ አገዛዝ የአገራችንን ህዝብ በዘር ከፋፍሎ ሲገዛ ቆይቷል።አሁንም በመግዛት ላይ ነው። በዚህ 22 ዓመት ውስጥ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የአገዛዙን ብትር በአንድም ሆነ በሌላ መልክ Read the rest of this entry

ኢ-ፍትሃዊነትን አንዋጋለን የከፋፍለህ ግዛት አስተዳደርን አንቀይራለን በሩንም በሰላም አናንካካለን ካልከፈቱልን ገንጥለን አንገባለን

ተሜን ለቀቅ ፕሮፖጋንዳችሁን ጠበቅ ጋዜጠኛም ሆነ የጥበብ ሰው ንሴብህ እያለ ከደለቀ አታሞ እውነት ስትጣራ ያልፋታል አርምሞ፡፡ ጋዜጠኛ ሲሆን የስርአቱ ቐሚ እውነት ስትጣራ አታገኝም ሰሚ፡፡ ይህ ግጥም ታደለ ገድሌ ትንቅንቅ በሚለው የግጥም መድብሉ አውነት ስትጣራ በሚል ርዕስ የከተባት ነች… Read the rest of this entry

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ወደ ዝዋይ ወህኒ ቤት ተወሰደ

Woubshet-Taye-Deputy-Editor-In-Chief-Awramba-Newspaperየአውራምባ   ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ወደ ዝዋይ ወህኒ ቤት ተወሰደ፡፡የአውራምባ   ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በፌደራል  አቃቤ ህግ በሽብርተኝነት ተከሶ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ጥፋተኛ በሚል 14 ዓመት ተፈርዶበት ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግበት ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ታስሮ ይገኝ ነበር፡.. Read the rest of this entry

የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኡሞድ ኡቦንግ ፕሬዚዳንትነታቸው ተነሱ

የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት በመሆን ለረጅም ጊዜ ያገለገሉት አቶ ኡሞድ ኡቦንግ ከክልል ፕሬዚዳንትነታቸው ተነስተው በፌደራል መንግስት መመደባቸው ታወቀ፡፡ ሰሞኑን በክልሉ በተካሄዱ ተከታታይ የስራ አስፈፃሚ…. Read the rest of this entry

ኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ የወጣት ክንፍ ድርጅት (ኢሕአፓ ወክንድ) የአውሮፓ ክፍል Ethiopian people’s Revolutionary party Youth League (EPRP YL) Europe Section

ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን አምርሮ የሚጠላው ጠባቡና ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርገውን የመብትረገጣ አፈና ግድያ ማስፈራራትና ወከባ ኢሕአፓ ወክንድ የአውሮፓ ክፍል በጥብቅ ያወግዛል። Read the rest of this entry

Demonstrated for Yalda and asylum children.

I’m here for Yalda, but also for myself.
A number of political parties and organizations highlighted yesterday their opposition to what they believe is a string of Norwegian asylum policy towards children. Abbas Saiadi (11) has lived in refugee centers Tromsdalen in three years. Read the rest of this entry

“የህወሀት ፈር የለቀቀ የበላይነት በዚህ አጋጣሚ ሊገታ ይገባል” ብአዴኖች የሥልጣን ሽኩቻ እና ሊፈነዳ የደረሰ ቂም

“የህወሀት ፈር የለቀቀ የበላይነት በዚህ አጋጣሚ ሊገታ ይገባል” ብአዴኖች የሥልጣን ሽኩቻ እና ሊፈነዳ የደረሰ ቂም

 የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ በኢህአዴግ ውስጥ የሥልጣን ሽኩቻ እና ሊፈነዳ የደረሰ ቂም እንዳለ በስፋት  ይወራል። እርግጥ ነው፤ ባለፉት ዓመታት በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በተለይም በህወሀት እና በብአዴን መካከል  ተዳፍነው የቆዩት የቂም እሳቶች በገሀድ የሚነድዱበት ጊዜ ላይ የደረስን ይመስላል።ስፍር ቁጥር ከሌላቸው  የነ አቶ በረከት እና የህወሀቶች ቁርሾዎች መካከል  ለዛሬ አንዱን እንመልከት። Read the rest of this entry

መንግስት በእስልምና ሀይማኖት ውስጥ የሚያደርገው ጣልቃ ገብነት በጊዜ ካልተገታ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚፈጠረው መዘዝ ተጠያቂ ነው ሲሉ በካናዳ ነዋሪ የሆኑ ሙስሊሞች ገለጡ

ህዳር 4 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-መንግስት በእስልምና ሀይማኖት ውስጥ የሚያደርገው ጣልቃ ገብነት በጊዜ ካልተገታ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚፈጠረው የሙስሊሞች መከፋፈልና በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ላይ ለሚያመጣው መዘዝ ተጠያቂ ነው ሲሉ በካናዳ ነዋሪ የሆኑ ሙስሊሞች ገለጡ::

ኦክቶበር 30፣ በቶሮንቶ አካባቢ የሚኖሩ በርካታ ሙስሊሞች ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ ባወጡት መግለጫ ፤ ”  የኢትዮጵያ መንግስት በፌደራል ሚኒስትሩ ቢሮ አማካኝነትና ሕዝብ ባልወከላቸው ግለሰቦች በሚመራውና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጠቅላይ ምክር ቤት ተብሎ በሚጠራው ቡድን አስተባባሪነት፤ በጥመቱና ከእስልምና መንገድ በመልቀቁ በዓለም ባለ የሙስሊሙ ኡላማወች  የተረጋገጠበትን የአሕባሽን አመለካከት፤ የመላ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መርህ እንዲሆን የሚደረገውን ጫና በጽኑ ተቃውመዋል።”

ሙስሊሞቹ ሰፊ ወይይት ካደረጉ በሁዋላ ባወጡት መግለጫ “መንግስት በሀይማኖት ውስጥ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም፣ የሙስሊሞች ጠቅላይ ጉባኤ ወይም መጅሊሱ የአህባሾች መሰባሰቢያ እንጅ የአብዛኛውን ኢትዮጵያዊ እምነት ብሶትና ፍላጎት አንጸባራቂ ባለመሆኑ መሪዎቹ ተሽረው ህዝብ በነጻ ምርጫ በመረጣቸው መሪዎች እንዲተኩ፣ መንግስት ችግር ፈጣሪ የሙስሊም ሀይሎች አሉ በሚልባቸው አካባቢዎች ከሀይማኖቱ ምሁራን፣ ከሙስሊሙ ሙያተኞች፣ እንዲሁም ከተለያዩ አገር ውስጥና ውጭ ካሉ የሙስሊም ድርጅቶችና የሙስሊም ማህበራት መሪዎች የተውጣጣ ስብሰባ እንዲጠራ” ጠይቀዋል።

መንግስት ” በሀይማኖቶች አለመቻቻል በአለም ታዋቂ ከሆነችው ሊባኖን አገር ሊቆች አመጣሁላችሁ ማለቱ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ብቻ ሳይሆን ለአገራችን ልእልና ደፋሪ ተግባር መሆኑ ታውቆ እንዲታረም እንጠይቃለን “፣ የሚሉት ሙስሊሞች፣ በአጠቃላይ የመንግስት እንቅስቃሴ የዜግነትን መብት የሚገፍ በመሆኑ አጥብቀው እንደሚቃወሙት ባወጡት መግለጫ ላይ ጠቅሰዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የኢትዮጵያን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሰካም።

ፍትህና ዲሞክራሲ በሌለበት አገር አልኖርም በሚል ምክንያት አንድ መምህር ራሱን በእሳት አጋዬ

ኢሳት ዜና:- በዋካ ከተማ ነዋሪ የሆነው መምህር የኔሰው ገብሬ   የስድስት ወረዳዎች ባለስልጣናት በአንድነት ተሰባስበው በቅርቡ በዋካ የተፈጠረውን ችግር በሚወያዩበት ወቅት፣  በራሱ ላይ ቤንዚን አርከፍክፎ እየተቃጠለ ወደ ስብሰባ አዳራሹ ገብቷል።

መምህሩ ራሱን እያነደደ ወደ ውስጥ ሲገባ የተመለከቱት የወረዳ ባለስልጣናት በመደናገጣቸው ከመምህሩ ለመራቅ ጥረት ያደርጉ ነበር ተብሎአል።

ምሁሩ በከተማው ውስጥ ከሚታወቁት በሳል ምሁራን መካከል አንዱ ነው የሚሉት የአካባቢው ነዋሪዎቹ፣  “ፍትህ እና ዲሞክራሲ በሌለበት አገር መኖር ሰልችቶኛል፣ በዚህ ሁኔታ በህይወት መቀጠል አዳጋች ነው” በማለት ይናገር እንደነበር ገልጠዋል።

መምህሩ በፖለቲካ አቋሙ ምክንያት ከስራ ተባሮ እንደነበር፣ በሁዋላም ወደ ስራ ለመመለስ ተደጋጋሚ ሙከራ አድርጎ እንዳልተሳካለት ታውቋል። በዋካ ከተማ ያለው ውጥረት አሁንም እንዳለ ሲሆን፣ በቅርቡ ለኢሳት መረጃ ሰጥተዋል ተብለው በጥርጣሬ የተያዙት ሰዎች አንዳንዶቹ በዋስ መለቃቀቸውም ታውቋል።

በአካባቢው የተሰማራው ልዩ ሀይል ግን አሁንም ከስፍራው አለመልቀቁን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።

በዋካ ከተማ ከወረዳና መብት ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ የተደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ “የህዝቡ ጥያቄ ፍትሐዊ ቢሆንም፣ መንግስት ግን አስፈላጊውን መልስ ሊሰጥ አልቻለም” በሚል ምክንያት፣ የቶጫ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ፈቃዱ ወልደሩፋኤልና  ፣ የዞኑ አቃቢ ህግ የሆኑት አቶ ከበደ ካሳ በራሳቸው ፈቃድ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል።