Daily Archives: May 4, 2012

ይድረስ ለአቶ መለስ አና እየገባቸው እንዳልገባቸው ለሚሆኑ አንባ ገነን የወያነኔ ባለስልጣናት በሙሉ።

 
 5/4/2012
Mosque inside the old city of Harar (Ethiopia).

Mosque inside the old city of Harar (Ethiopia). (Photo credit: Wikipedia)

ኢትዮጵያዊ  የመሆን  ሁኒታችን  አያጠራጠረ  ከመጣ  ብዙ   አመታቶችን  እያስቆጠርን  ይመስለኛል   ምክንያቱም  ኢትዮጵያዊ ማለት  በናንተ   አመለካከት    በአንድ  ፓአርቲ  ወይንም  የወያኔ  አባል ያልሆነ  ሁሉ  ኢትዮጵያዊ  መስሎ   አይታያችሁም ፤ወደ ቁምነገሩ  ልግባና  መንግስት  እንዴት  ነው  የሙስሊሙ  ጥያቂ  አልገባ  ያለው  ሁሌም   በሚሰጠው  መግለጫ  ብሎም በአቶ   መለስ  አንደበት  ስሰማው   የሚመልሱት  ሌላ  የተጠየቁት  ሌላ  ይህ  አይነት  አሰራራቸው  የተለመደ  ቢሆንም   የአሁኑ   የሙስሊሙ  ጥያቄ  ግን  አንድና  አንድ  ነው፡፡እሳቸው   ወይንም   አብሮዋቸው  የሚሰሩ  ሆድ   አደሮች  ሙስሊሙ  ለጠየቀው  ጥያቄ   መልስ  መስጠት  ሳይሆን  ለሙስሊሙ ህብረተሰብ  ሌላ  ጥያቄን  በጥያቄ  የመለሳችሁ  ነው  የሚመስለው  ጥቂቶች  ናችሁ  የሚል  ነበር   ሙስሊሙ  ህብረተሰብ   ግን እርሶና  አበሮቾ  ለጠየቁት  ጥያቄ   አፋጣኝ  ምላሽ  ተሠጦት   ብዙ ሚሊዮን  መሆናችንን  በተግባር  አሳይተናል ፡፡እዚጋ  አንድ  ያልገባዎት  እና  ያልተረዱት  ነገር  ያለ  ይመሰለኛል  የስልጣን  እድሚዎትን  ለማራዘም  የዘር ክፍፍል  ተጠቅመዋል  ይህ  እስትራቴጅ  ግን  ለሀይማኖት  ግን  መጠቀም  የማይታሰብ  ነው፡ያም ሆነ ይህ በሀይማኖት ውስጥ ጣልቃ መግባት  እድሜን ለማራዘም  ሳይሆን  እድሜን  ለማሳጠር  ስለሚያጋልጦ  አንድም  ቀን ብትሆን  እድሜ  ናትና  ለጉዳዩ  አስቸኩአይ መልስ  መስጠት ተገቢ ነው  እላለው፡ሙስሊሙ  ህብረተሰብ  ለጥያቄው መልስ  እስካላገኘ ድረስ  100 ሺ ግዜ  መግለጫም ሆነ  አለኝ  ብለው  የሚተማመኑበትን  ጦር  አምጥተው  ቢደረድሩ  እኛ  ሙስሊሞች  ከአላማችን  ያንዲት ነጥብ ያክል ወደውሀላ አንልም ጥያቄአችን አሁንም  ቢሆን  እደግመዋለው  አልገባ  ካልዎት  ደጋግመው  ያንብቡት፡እርሶ  ሲገቡ  ከርሶ  ጋር  ተከትሎ  የገባ  በእስልምና  ሀይማኖት  የሚነግድ  አህባሽ  የሚባል  ቫይረስ  ከላያችን ላይ ይውረድ  ነው ጥያቄአችን  ይህ  ቫይረስ  የራሱን እምነት የማስፋፋትም ሆን የማስተማር መብቱ የተጠበቀ  ሲሆን  ይህን ማድረግ  የሚችለው  ግን በኛ  በሙስሊሞች  መስጅድ  ት/ቤት   ሸሪያ  በመሳሰሉት  በማንኛውም  ነገር  እኛን  ሙስሊሙሞችን ሊወክለን  አይችልም ፡ከሙስሊሙ  ህብረተስብ  ውጪ መንቀሳቀስ  ይችላል  እንደሌላው  ሀይማኖት  እራሱን  ችሎ፡   እንግዲ  ጥያቄአችን  ይህንን ይመስላል፡ ሙስሊሙ  ህብረተስብ ህግ እና  ደንብን  በማክበር  ይመስለኛል  ተቃውሞአችንን  በመስጅዶቻችን  ውስጥ እያሰማን  12 ኛ ሳምንታችንን   ያስቆጠርነው፡ ኢቲቪ  4/4/2004  መግለጫ  ብሎ  በተናገረው  ላይ  የመንግስት  ዝም ማለት  ፍርሀት   እንዳይመስላችሁ    በማለት ተናገሮአልእናንተስ  የሙስሊሙ ህዝብ  በመስጅድ  ውስጥ ታአፍኖ ተቃውሞ  ማድረግ  ፍርሀት  ይመስላችሁ ይሆን  ?               እንደዛ አስባችሁ ከሆነ በጣም ተሳስታችሀል ፡ ማንኛውም ሙስሊም በሀይማኖቱ ለሚመጣበት ነገር ህይወቱን ከመስጠት ወደውሀላ እንደማይል ልትገነዘቡ ይገባል   ፡ ይልቁንስ ባጣዳፊ  ሁኔታ መልስ  መስጠቱ ጠቃሚ ነው ብዪ  እገምታለው።
ከኡስማን አ/ሰመ

በአቶ መለስ መንግስትና በኢትዮጵያ ሙስሊሞች መካከል የተፈጠረው ውጥረት አደገኛ ደረጃ ላይ ደርሷል

Friday, May 4, 2012
ኢሳት ዜና:-

የብዙሀኑ ሙስሊም አስተባባሪ ኮሚቴ፤ “በሀሰት ፕሮፓገጋንዳ የመብት ጥያቄዎቻችን አይዳፈኑም”  በሚል ርዕስ ባለ 15 ገጽ መግለጫ በበተነበት በትናንትናው ዕለት፤ መንግስት  በፊናው የማስጠንቀቂያ እና የማስፈራሪያ መግለጫ አውጥቷል።
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ባወጣው በዚሁ ረዥም መግለጫ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ   በአብዛኛው የሙስሊም ህብረተሰብ ዘንድ እየተነሳ ያለውን ጥያቄና ተቃውሞ፤ በምርጫ 97 ወቅት ተከስቶ ከነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር አመሳስሎታል።
“መንግስት  ለእስልምና እምነትና ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ካለው አክብሮት በመነሳት  እያሳዬ ያለው ሰፊ ትዕግስት፤ የተቃውሞው አስተባባሪ የሆነው  ህገ ወጥ ሀይል  ከፍርሀት እየተመለከተው  ነው” ሲልም- የአቶ መለስ መንግስት አለመፍራቱን ጠቅሷል። Read the rest of this entry