Daily Archives: May 23, 2012

ክፉ ዓይን አየን! “ክፉእ ርኢና!” – ከጌታቸው ረዳ

Published On: Wed, May 23rd, 2012
 
 አሜሪካ ውስጥ “ካምፕ ዴቪድ በተባለው የተከበረ የመሰብሰቢያ አዳራሽ” ባለፈው ሰሞን “ቡድን 8” ተብሎ የሚጠራው የሞገደኛ አገሮች የምጣኔ ሃብት ጉዳይ ውይይት ስብሰባ ውስጥ “ለማጣፈጫ” ተብለው ከተጋበዙ ጥቂት ኮስማና የአፍሪካ አገሮች መካካል አንደኛዋ ኢትዮጵያ ስትሆን በወያኔው መሪ “መለስ ዜናዊ” ተወክላ ነበር። ታዲያ በዛው አዳራሽ ውስጥ የመለስ ዜናዊ “የሕሊና ሱሪ እና ውስጣዊ ጤንነቱን” የሚፈታተን በዚህ መጣ ያልተባለ ማንም ያልጠበቀው ድንገተኛና መብረቃዊ የተቃውሞ ድምፅ ሲስተጋባ “ፓኒክ አታክ” ተብሎ በሕሊና ሓኪም ተመራማሪ ሊቃውንቶች የሚጠራው የፍርሃት ሰመመን መለስ ዜናዊ አጥንት ውስጥ ገብቶ ለአንድ ደቂቃ ያክል ሕሊናው በመሳቱ፤ “አንገቱ ወደ መሬት ደፍቶ፤ዓይኑን በእንቅልፍ ሰመመን በግድ ሲከፍትና ሲዘጋ፤ Read the rest of this entry

አሳዛኝ ዜና እህታችን ፍርዶስ በ ዶ/ር ሽፈራዉ የድህንነት ሀይሎች በደርሰባት የ ኤሌክትሪክ ሾክ እና ድብደባ ከዚህ አልም በ ሞት ተለየች!

Published On: Wed, May 23rd, 2012
አሳዛኝ የግፍ ዜና ኢናሊላሂወኢና ኢለይሂ ራጂኡን በሴት ሙስሊሞች ላይ የሚደረሰዉ ግፍና መከራ እንደቀጠለ ነዉ:: ይህም የግፍ ዜና ምንጮቻችን እንደዘገቡልን እናቀርበዎል:: ጉዳዩ እንደሚከተለዉ ነዉ በቅርቡ የፌደራል ጉዳዮች ከየክፍለ ከተማዉ የተመረጡ ሰዎችን በመጥራ ስብሰባ አካሂዶ ነበር:: በዚህም ስብሰባ ላይ ከኮልፌ ክ/ከተማ ሶስት ሰዎች የተሳተፍ ሲሆን ሁለት ወንድ እና አንዲት ሴት ይገኙበታል:: Read the rest of this entry

የአንድ ለአምስት ፖለቲካዊ አደረጃጀት ወደ መንግስት መ/ቤቶች እየዘለቀ ነው

may 24,2012 

ኢሳት ዜና:- ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የፌዴራል የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሠራተኞቹን አንድ ለአምስት በሚል አደረጃጀት በማዋቀር በሥራ ሰዓት ጭምር ስብሰባዎችን በማካሄድ ሠራተኛው እርስ በርስ እንዳይተማመን የማድረግ አሠራር ተግባራዊ በማድረጉ በሥራ ዋስትናቸው ላይ ከፍተኛ አደጋ መጋረጡን አንዳንድ ሠራተኞች አስታውቀዋል፡፡
 
ባለሥልጣኑ ከቅርብ ግዜ ወዲህ የልማት ሠራዊት ለመገንባት በሚል ሠራተኛው አንድ ለአምስት እንዲደራጅና በየዕለቱ ከ30 ደቂቃ ላላነሰ ግዜ በቀኑ ውስጥ ባጋጠሙ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት በሚል ሰበብ ስብሰባ እንደሚቀመጥ ሰማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ሠራተኞች ተናግረዋል፡፡ Read the rest of this entry