Daily Archives: February 14, 2013

የእሁድ ምሽት ከታማኝ የኦስሎ የኢሳት ገቢ ማሰባሰብያ መርሃ ግብር ጋር

Ethiopian satellite television, norway
የዛሬዋ የእሁድ ምሽት ከታማኝ የኦስሎ የኢሳት ገቢ ማሰባሰብያ መርሃ ግብር ጋር ያሳለፍኩት ምሽት ነበር። ምንም እንኳን መርሃግብሩን በሙሉ ለመፈፀም ባልችልም የአክትቪስት እና አርቲስት ታማኝን በቪድዮ የተደገፈ ገለፃ ግን ለመከታተል እድሉ ገጥሞኛል።
ኦስሎ ለኢሳት ገቢ ማሰባሰብያ መርሃግብር ከተገኘው ሕዝብ በከፊል (photo GUDAYACHN BLOG EXCLUSIVE)
ገብስማ ፀጉሩ ከነጭ ሸሚዝ እና ሽሮ መልክ የያዘ ክራቫት ጋር ታማኝን ግርማ ሞገስ አጎናፅፎታል። Read the rest of this entry

ሲኖዶሱ እና መጅሊሱ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ማጥመቂያ? በተመስገን ደሳለኝ

ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ ሼህ፣ ኢማም፣ ኡላማ፣ ደረሳ፣ ፓስተር፣ ዘማሪ፣ ካድሬ፣ ጠርናፊ፣ ተጠርናፊ፣ ሊግ፣ ማህበር፣ ፎረም፣ ግንባር ቀደም አርሶአደር፣ ልማታዊ ባለሀብት፣ ልማታዊ ጋዜጠኛ፣ ልማታዊ አርቲስት፣ ልማታዊ ማስታወቂያ ሰራተኛ፣ ልማታዊ እድር፣ ልማታዊ ማሀበር፣ ልማታዊ… ማን ቀረ? ማንም፡፡ እናም በዛሬ ጊዜ እመንም አትመንም የእነዚህ ሁሉ ምንጭ መለስ እና ኢህአዴግ ናቸው፡፡ Read the rest of this entry